ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 9

ቀጥሎ ደግሞ ክለብ ስሰራ ብዙ ልምዶችን ስላገኘው ቀጥታ ሙዚቃዎቼን ሪኮርድ ወደማድረጉ ገባሁ ማለት ነው ። የመጀመሪያ ስራዬ “ አስኮቱ ” እሱም በጣም ጥሩ አቀባበል ነበረው ፡ ከዛ ቀጥሎ ደግሞ “ ሳላይሽ ” ን ሰራሁ አቀባበሉም ጥሩ ሆነ እግዚሐብሄር ይመስገን በስራዎቼ ሁሉ ደስተኛ ነኝ ። •

የ አውደብሩሀን ገጾች

ቅንድል ሀይሌ የመምህር ልጅ ነው ታድያ የመምህር ልጅ መሆነህ የተለየ የጠቀመህ ነገር አለ በህይወትህ ?
ሀይለየሱስ አዎ የመምህር ልጅ ነኝ ። በርግጥ ሁሉም ቤተሰብ መምህር ባይሆንም ለልጁ የሚሰጠው የሚጠቅም ነገር ይኖረዋል ነገር ግን የመምህር ልጅ በመሆኔ የተሻለ ነገር ይዤ ወጣሁ የምለው የማንበብ ልምድን ነው ። ለኔ ማንበቤ ብዙ ጠቅሞኛል ከምነግርሽ በላይ አባቴ የአሁን ማንነቴ ላይ እንድደርስ በደንብ ለፍቶብኛል ።
ቅንድል “ የአዲስ ቀን ፀሀይ ” አልበም ለመስራት ከነበረው ችግር በላይ ለህዝብ ለማቅረብ ብዙ ነገሮችን እንዳለፈ በብዙ ቃለ መጠይቆች ገልፃል የነበረውን ነገር በጥቂቱ አውራን እስቲ ? እንዲሁ ህዝብ ጋር የነበረውን አቀባበልም እንዴት ነበር የልፋትህን ያህል አግኝተሃል ?
ሀይለየሱስ እእእ እውነት ለመናገር አዎ ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩ ግን ያው ሰርቶ ስለማቅረብ ስናወራ ብዙ እንቅፋቶች እንደሚኖሩት ግልፅ ነው ። አልበም ስትሰራ ደግሞ እንዴት ሊከብድ እንደሚችል መገመት ቀላል ነው ። ለኔ በወቅቱ ዘፈኑን ሰርቼ ህዝቡ ጋር ለማድረስ ብዙ ውጣ ወረዶችን አልፌያለሁ ግን አሁን ስሰማው እንኳን ሆነ እንኳን ለፋሁበት ነው የምለው ። ስለአቀባበሉ ስናወራ ደግሞ የልፋት ያህል ብለሽ መጠን የምታስቀምጭለት ነገር አይደለም ፡ በተመሳሳይ የደስታ መጠን ብለሽም ገደብ ልታበጂለት አትችይም ግን በጠበኩበት መጠን ሳይሆን እኔ እንድሰራው ፈልጌ ወደመሬት አውርጄ የሰራሁት ነገር ለህዝብ ደርሶ እኔ ራሱ ስሰማው ያለመሰልቸቴ ሰዎች ሲሰሙት ሳይ እረካለሁ ያ ነው የኔ ትርፍ የማልፀፀትበትን ነገር መስራት መቻሌ ።
ቅንድል አርያዬ ነው የምትለው ሰው አለህ ? ምክኒያትህስ ?
ሀይለየሱስ አባቴ ለኔ አርያዬ ነው ። እኔ አሁን ባለሁበት እድሜ ሆኜ የሆነ ትልቅ ሀላፊነት ወስደህ በውስጥ የሚፈታተኑህን ችግሮች አልፈህ ፡ ቢከፋህ ቢጨንቅህ ብትቸገር የችግሮችህ ማለፊያ እንዲሆን ሌላ ነገር መስራት ስትችል ይሄን ከማን ተምሬው ነው ትያለሽ አይደል ? እኔ ከአባቴ ነው የተማርኩት ፡ አባቴ ያለ እናት ነው ያሳደገን ለሚፈጠሩት ፈተናዎች ሁሉ መፍትሄ የሚያደርጋቸው ነገሮች የሚደንቁ ነበሩ ፡ አንዱ ወደቤተክርስቲያን መሄድ እንደነበር አስታውሳለሁ ። እኔ አድጌ አሁን ስመለከተው እሱ በዛ ጊዜ ተቋቁሞ ያለፋቸው ነገሮችን ሳስባቸው ጀግና ይሆንብኛል ። አሁን ሰዎች ሲጨንቀቸው ወደሚያደርጉት አላስፈላጊ ነገሮች ውስጥ የመግባት ምርጫ ነበረው አባቴ ግን ምርጫውን ግን ወደዛ አላደረገም ሁሉን ፈተና አልፎ መልካሙን መንገድ መርጧል ። እና ለኔ አርያዬ እሱ ነው ።
ቅንድል በዚህ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ እንደማንኛውም ባለሞያ ከባዱ ነገር ምንድነው ትላለህ ? አንተን ፈትኖህ የነበረ ነገር ካለም አካፍለን ለሌሎች እንዲሆን ?
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 9