የ አውደብሩሀን ገጾች
ሰላም የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የቅንነት ዘማሪ ፣ የምክንያታዊነት ምልክት ፣ የሀገር ፍቅር ማሳያ የሆናችሁ ባለራዕይ የቅንድል ዲጂታል መጽሄት አንባቢያን ፡፡ እንደሚታወቀው በአውደ ብሩኃን ገጻችን በሀገራችን ኢትዮጲያ በኪነ-ጥበብ ፣ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በማህበራዊ ግልጋሎት ፣ በበጎ አድራጎት ፣ በስፖርትና በሌሎች የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለሀገራቸው በርካታ ትሩፋትን ያበረከቱና ቅንነትን መለያቸው ፣ ምክንያታዊነትን የህይወት መርህ አድርገው በሀገር ፍቅር ከተቃኙ መካከል ለእናንተ ለአንባብያን በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ከህይወታቸው ፣ ከስብዕናቸው ፣ ከስራ ውጣ ውረዳቸውና ከትዝብታቸው ትማሩበታላችሁ ያልናቸውን ወደእናንተ የምናደርስበት አምድ ነው ፡ ፡ ታዲያ በዛሬው የዐውደ ብሩኃን ገጽ እንግዳችን ድምፃዊ ሀይለየሱስ ፈይሳ ነው ፡፡ ሀይለየሱስ ፈይሳ ከጥበብ ትርፋቱ ፣ ከህይወት ልምዱ ሊያካፍለን ከነፃነት ጌታቸው ጋር ቆይታ አድርጓል ፡፡ እንድትከታተሉን አስቀድመን በትህትና እንጠይቃለን ፡፡
ቅንድል በመጀመሪያ ሀሳባችንን ተረድተህና ደግፈህ ቅንነግ በሚሰበክበትና ስኬታማ ሰዎች ልምዳቸውን በሚያካፍሉበት መፅሔታችን እንግዳ ለመሆን ፍቃደኛ ስለሆንክ በቅንድል መፅሔት አዘጋጆችና በውድ አንባቢዎቻችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።
ሀይለየሱስ በእውነት እናንተም እንግዳችሁ እንድሆን ስለመረጣችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ። እግዚሐብሄር ያክብርልኝ ።
ቅንድል እንደው ወደዋናው ጥያቄዎቻችን ከማለፋችን በፊት ለአንባብያን እራስህን ብታስተዋውቅልን ? ሀይለየሱስ የት ተወለደ ? የት አደገ ? ልጅነትህ ምን ይመስል ነበር ? አንተ ባደክበት አከባቢ አንድነታቸው ፍቅራቸው በደጋገፋቸውን እግረ መንገድህን አስታውሰህ ብታጫውተንም ደስ ይለናል ።
ሀይለየሱስ ድምፃዊ ሀይለየሱስ ፈይሳ እባላለሁኝ ። ከሙዚቀኛነት ባለፈ የግጥምና የዜማ ደራሲም ነኝ ። የተወለድኩት ደሴ አከባቢ ነው ። ያደኩት ግን እዚሁ አዲስ አበባ ነው ። እንግዲህ ብዙዎቻችን ያደግንበት ማህበረሰብ የመጀመሪያ ትምህርት ቤታችን ነው ።
ለደስታ ለሀዘንም በመጠራራት ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችን ላይ እንድንበረታ ፣ የጎረቤትን ችግር እንደራስ በመቁጠር ህመም ፈጣሪዎች ሳይሆን ህመም ተጋሪዎች እንድንሆን ፣ መከባበርን እና መዋደድን ከጥላቻ ብዙ እጥፋ አብልጠው ያስተማሩን ናቸው ። እኔ የማውቀው ያደኩበት ማህበረሰብ እንደዚህ ነበር ። ልጅነቴም ሁላችንም ልጅነታችንን በምናሳልፍበት መንገድ ነው ያሳለፍኩት አንደኛ ደረጃ ትምህርቴን ,,,,,, ተማርኩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ደግሞ አዲስ ከተማ ነው የተማርኩት እንደዚህ እንደዚህ እያለ እየተኖረ ነው እንግዲህ ።
ቅንድል መጀመሪያ ወደ ሙዚቃው ኢንዱስትሪ የገባህበት አጋጣሚ እንዴት ነበር ? ስራህና የአድማጮች አቀባበልስ እንደጠበከው ሆኖልህ ነበር ?
ሀይለየሱስ እምምምም በእውነት ወደ ሙዚቃ የገባሁበትን ትክክለኛ አጋጣሚ በትክክል አላስታውስም ። ግን ከልጅነቴ ጀምሮ በተማርኩባቸው ትምህርት ቤቶች እዘፍን እንደነበር አስታውሳለሁ ከዛ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ወደ ሙዚቃው ስቀላቀል ግን እንደማንኛውም
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 8