ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 10

የ አውደብሩሀን ገጾች

ሀይለየሱስ ሙዚቃ በጣም ከባድ ነገር አለው ። በአምስት ደቂቃ ተከፍቶ እንደሚሰማው ቀላል ነገር አይደለም በጣም ከባድ ነው ። ይቺ የአምስት ደቂቃዋን ዘፈን ለመስራት ብዙ ጉዜ ይፈጃል ብዙ አቅም ቀንዘብ ይጠይቃል ። ከብዙ ልፋት በኋላ አልቃ ሰዎች የሚያዳምጧት የአምስት ደቂቃ ሙዚቃ ተከፍቶ እንደሚያልቀው አይነት አስተላለቅ አይደለም ተሰርታ ያለቀችው ። ያምራል ተሳካለት ቆንጆ ዘፈን ሆነ የሚለው ግን በዛች ድካም ውስጥ ያለ ነገር ነው ። እሯጮችን የሚለያቸው መጨረሻ ላይ ያለችዋ ደቂቃ አይደለች ? በሙዚቃው አለምም ለፍተሽ ለፍተሽ መጨረሻውን ለማሳመር መጋጋጥ ግድ ይልሻልና እሱ ላይ በደንብ መስራት ይጠይቃል ።
ቅንድል አሁን ሁላችንም እንደምናውቀው እንደሀገር የተጨነቅንበት ጊዜ ላይ ነን እንደው ይሄን ውጥንቅጥ ባሰብክ ጊዜ ምንድነው የሚሰማህ ? የሙዚቀኛ ድርሻው ምንድነው ትላለህ ? እንደዚህ ትውልድ አካል ምን ብናደርግ ብለህ ታስባለህ ?
ሀይለየሱስ እምም ያው አሁን እየገጠሙን ያሉ መከራዎች ሁሉ የአዲስ ቀን ፀሀይ ነው ብዬ አስባለሁ ሊነጋ ሲል የሚጨልም አይነት ነገር ነው ። ከዚህ ውጪ ግን ክፉና ደጉን መለየት በሚከብድበት ጊዜ ላይ ነን ያለነው ለዚህም መፍትሄው ፀሎት ነው መፀለይ አለብን ። ከዛ በተረፈ ግን በነዚህ ጊዜዎች ላይ አንድ ሆኖ በፊት የነበረችውን ኢትዮጵያ እንደነበረች ለማቆየት በአሁኑ ሰዓት ላይ ትልቁ የሚያስፈልገው ነገር አንድነታችን ነው ። በአንድነት የመዘመር ልምድ ያስፈልገናል ። አርት በጣም ትልቅ መሳሪያ ነው ነገቆችን ለመለወጥ ስለአንድነት ቢዘመር ስለአንድነት ቢዘፈን ስለኢትዮጵያዊነት ቢዘፈን በዚህ ሰዓት ላይ አስፈላጊና ቦታውም ነው ብዬ አስባለሁ ።
ቅንድል ሀይለየሱስ ሙዚቀኛ ባይሆን ምን ይሆን ነበር ? ሰው የማያውቀው ሌላ የተለየ ተስጦ አለህ ?
ሀይለየሱስ ሙዚቀኛ ባልሆን ኖሮ ጠበቃ እሆን ነበር ፡ አሁን ግን የጀመርኩትን መንገድ ነው የምጨርሰው ።
ቅንድል ኢትዮጵያዊነት ማለት ላንተ ምን ማለት ነው ? የሀገር ፍቅርስ ?
ሀይለየሱስ ኢትዮጲያዊነት ለኔ ? ማንነት ነዋ ደሜ ! የሀገር ፍቅር የሚገለፀው በቤተሰብ በአከባቢ በመዋደድ በመከባበር ነው ። ሀገር የሚባለው ትልቅ ነው የሚጀምረውም ከቤት ነው ። የቤተሰቦቻችን ራስ እናቶቻችን ወይን አባቶቻችን የቢቶቻችን አለቆች ወይንም በሀገር ደረጃ እንደምንለው ጠቅላይ ሚኒስተሮች ናቸው እነሱ በሚያስተዳድሩት ቤት ላይ የአስተዳደር ችግር ካለ ያ ነገር አድጎ ሀገር ይጎዳል በተመሳሳይ አስተዳደጋቸው አይንም አስተዳደራቸው መልካም ከሆነ ሀገር ይሰራሉ ማለት ነው ። የሀገር ፍቅር አጠገባችን ባለው ሰው ላይ በምናደርገው ነገር ይገለፃል ። የሀገር ፍቅር በልባችን በምናስበው ጥሩና መልካም ነገርም ይመዘናል ከልብ የሚሰፋ የት አለ ? ሀገራችንን የምንወድ ከሆነ ከራሳችን ነው መጀመር ያለብን ብዬ አስባለሁ ።
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 10