ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 11

የ አውደብሩሀን ገጾች

ቅንድል በአዲሱ ዓመት ከሀይሌ ምን እንጠብቅ ? አዳዲስ ስራዎች እጅህ ያሉ ይመስለኛል መች እንጠብቅ እነሱንስ ? የፍቅር ንቅሳት ብለህ መጠሪያ የሰጠኸው አዲስ ነጠላ ዜማ ከሰሞኑ ልትለቅ ነው ። የፍቅር ንቅሳት ስትል ምን ማለትህ ነው ?
ሀይለየሱስ በአዲሱ ዓመት እንግዲህ “ የፍቅር ንቅሳት ” አንዱ ነው ። በመንግስት ደረጃ የመጣ 28-ትራኮችን የያዘ ብዙ አርቲስቶች የተሳተፉበት አልበም በቅርቡ ይመረቃል ። እዛ ላይ “ ሀገርና ሚስት ” የሚለውን ግጥምና ዜማ በመስራት እንዲሁም አብሬ በመዝፈንም ተሳትፌያለሁ ። የፍቅር ንቅሳት ሀሳቡ ምን መሰለሽ ,,,,, እንግዲህ ስንጓዝ አብረን ተገጫጭተን ፣ ተገፋፍተን ፣ ተመታተን ፣ ተሰዳድበን ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለነገ ለሚሆን ጥሩ ምኞት ያኛው የቆሰልነው የደማነው የተሰበርነውን ስብራታችንን የፍቅር ንቅሳት አድርገነው ወደፊት እንጓዝ የሚለውን የያዘ ነው ።
ቅንድል ፦ አርቲስቶች ሰብሰብ ብላችሁ በጋራ አዲስ አልበም እንደሰራችሁ እየተነገረ ነው እስቲ ስለሱ አውራን ? ያንተስ ተሳትፎ ምንድነው ? ሰብሰብ ብሎ አልበም የመስራት ሀሳቡስ እንዴት መጣ ?
ሀይለየሱስ ፦ አልበሙ በመንግስት ደረጃ የመጣ ነው አንድ አይነት ህብረትን ለመፍጠር በመፈለግ ፡ እና እኔም ሀሳቡ ሲነገረኝና እንድሳተፍ ስጠየቅ
በደስታ ነው የተቀበልኩት ፡ ቅድም እንዳልኩሽ “ ሀገርና ፍቅር ” የሚለውን ግጥምና ዜማውን በማዘጋጀት አብረውኝ ከሚያዜሙ ጓደኞቼ ጋር ጥሩ አድርገን ሰርተነዋል ቀጣይ ሳምንት ይወጣል ብዬ አስባለሁ ።
ቅንድል በመጨረሻ እኛ ቅንድሎች ቅን ምክኒያታዊ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የተለያዩ መልካም ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ። በዚህ አጋጣሚ ለኛም ለወጣቶችም የምታስተላልፈው መልዕክት ካለ እድሉን ልስጥህ ?
ሀይለየሱስ ፦ በዚህ ሰዓት ላይ እንግዲህ እንደወጣት በነገሮች ሁሉ ስሜታዊ ሳንሆን በተረጋጋ መንፈስ ለሚሰማውም ለሚታየውም ነገር ሙሉ የሆነ ግምት እየሰጡ ውሳኔዎችን ከመወሰን ተቆጥበን የምናደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ በማስተዋል እና በመጠንቀቅ እናድርግ ለማለት እፈልጋለሁ ። እናንተም እየሰራችሁ ያላችሁት ነገር በቀላሉ የሚታይ አይደለም የሀገር ባለውለታ ናችሁ ለነገዋ ብረሃን እያቀበላችሁ ያላችሁት መልካም ነገር ትንሽ አይደለምና በርቱ ከጎናችሁ ነን ።
ቅንድል ፦ እኔ ጨርሻለው ሀይሌ በድጋሚ የቅንድል ዲጂታል መፅሔት እንግዳችን ስለሆን ከልብ እናመሰግናለን ።
ሀይለየሱስ ፦ እኔም አመሰግናለሁ ።
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 11