እንኳን ለ2014 ዓመተ ምህረት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን ! በአሉን ስናከበር ቅንነትን በተግባር ፣ ምክንያታዊነትን በህይወት ፣ ሀገር ፍቅርን በመኖር በጉዟችን እናንግስ ። ሰላም ከኛ ይጀምራልና ልባችን በሰላም ይፅና ፣ ነጋችን በዕቅድ ይጀመር ፣ አብሮነታችን በፍቅር ይታደስ ፣ በሁሉም ዘርፍ እንክበር ፣ ተርፎን የምንቸር ብቻ ሳይሆን ካለን የምናካፍል ያድርገን ። እንደ ቀዬው በውብ ገፅ የፈካ ህይወት ፣ እንደ መስከረም ወር ብርሀን የሆነ ግዜ ፣ የጥላቻ ፍፃሜ ይስጠን ። ሀገራችን ከቢጫ ወርቅ የደመቀ ምንስ ውበት ሊኖራት ፣ በፀጋ የተሸለመ 13 ወር ተሰቶናልና በመታደስ ፣ በመፅናት ፣ በመታዘዝ ፣ በመባረክ እንኑረው ። ደስታ በቤታችን ሰላም በሀገራችን ፤ ፍቅርን ለሰው ልጆች ሁሉ ፈጣሪ እንዲሰጥልን የቅንድል ዲጂታል መፅሔት የዝግጅት ክፍል ይመኛል ፡፡ ቅን ምክንያታዊ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያ !
# ቅንነትድልያደርጋል ቅንድል ዲጂታል መፅሔት