ዝና ፣ ሀብት ፣ ክብርና ሽልማት ጥሩ ትከሻና ህሊና የሌለው ሰው ሊሸከማቸው ብቻ የሚችል ብርቱ ሰው ነው ፡፡ ጥንካራ ስራ ፣ ስነ-ምግባር ፣ ጥረትና ሀገር ፍቅር የሱ መለያ ናቸው ፡፡ አይደለም ተከፍቶ ተደስቶም የሀገሩ ስም ሲጠራ እምባው ይቀድማል ፡፡ በሀገረ ሆላንድ ከመከበር አልፎ እንደ ምሳሌ የሚጠራ ልዑል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ በሱፍም በቁምጣም ስኬት እጁ ላይ ነች ለዚህ ደሞ ሚስጥሩ ስራ ወዳድነቱ ብቻ ሳይሆን ጥረትን ከስኬት ጋር መዝኖ መኖር የሚችል ብርቱና ልባም ሰው በመሆኑ ነው ፡፡ ከ28 በላይ ሪከርዶችን በአለም መድረክ በኢትዮጲያ ስም የግሉ አድርጓል ፣ ከኦሎምፒክ መድረክ እስከ ግል ውድድሮች የማይዝሉት ጉልበቶቹ በአውሮፓ ጎዳናዎችና እስቴድየሞች ተመስክሮላቸዋል ፤ ከያንያንን ሳይቀር ያስደመሙ ጉልበቶች በአንድ ሌሊት ግጥምና ዜማ ተሰናድቶላቸው ለክብሩ ተሰጥተዋል ፡፡ ይህ ሰው ሀይሌ ገ / ስላሴ እንደሆነ ማንም ይመሰክራል ፡ ፡ እሱ በቢዝነሱም አለም በተለይ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለበርካታ ኢትዮጲያውያን የሰራ እድል መፍጠር የቻለ ባለ ብዙ ክብር ባለ ብዙ ስራ ባለቤት ነው ፡፡ ቅንድል ዲጂታል መጽሄት በዛሬው የአዲስ አመት ልዩ ዕትም ይህን የሀገር ኩራት የቅኖች ምሳሌ ስትል ለሀገር የዋለውን ውለታ በማስታወስና አሁንድረስ ለብዙ ዜጎች በተለይም ለወጣቶች ምሳሌ ሊሆን የሚችል ስራ በመስራቱ ቅንነትን በስራውና በኑሮው ምክንያታዊነቱን በስራው ፣ ሀገር ፍቅሩን በተግባር ለኖረበት ባለ ውለታነቱ አመስግነናል ፡፡ ደስታን ከሚናገረው ፈገግታውና ስኬቱ ጋር ለሀገር ብዙ ቀሪ ትሩፋት እንዲሰጥ አደራ እያልን እድሜና ጤና ተመኘን ፡፡
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 13