አዕምሮ ጤና
ምልክቶቹ 1- ለአሰቃቂ ነገር ተጋላጭ ከሆኑ በኋላ የሚፈጠር ነው ። በራሳቸው ለይ የተፈጠረ ገጠመኝ ሲሆን ፣ ሌሎች ሰዎች ለይ ሲደርስ መታዘብ ፣ በቤተሰብ አባል ለይ መድረሱን ሲያዉቁ ፣ እና ተደጋጋሚ አጋላጮች ሲኖሩ ( የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ) 2- ተመላላሽ ፣ ጣልቃ ገብ የሆነ የሚረብሽ ትውስታ ፣ ቅዠት ፣ ሰመመን ዉስጥ መግባት ። አደጋው እንደ አዲስ በእዉን የሚፈጠር ይመስላቸዋል ፣ ሁኔታዉን እንደነበረው ይተገብሩታል ፣ ፍንጭ የሚሰጡ ነገሮች ( ሲሰሙ ፣ ሲያዩ ) ይረብሻቸዋል ። 3- የጸና ሽሽት ውስጥ ይገባሉ ። ስለሁኔታው ትዉስታ የሚሰጣቸውን ላለመስማት ፣ ላለማየት ፣ ሰዎችንም ላለማግኘት በጽናት ይሸሻሉ ። ትውስታውንም ለመርሳት ሱስ ይጠቀማሉ ። 4- አሉታዊ አስተሳሰብ እና ስሜት ይኖራቸዋል “ እኔ መጥፎ ነኝ ፣ ማንም ሰው አይታመንም ፣ አለም ክፉ ናት ” የሚሉ አስተሳሰቦች በግለሰቡ ለይ ይነግሳሉ ። እራስን መውቀስ ራስን ለማጥፋት ሲገፋፋ ፣ ሌሎችን መውቀስ ደግሞ ለከፋ የአዕምሮ ጤና መታወክ ፣ ሱሰኝነት ብሎም ክፋት ይዳርጋል ። ፍርሃት ፣ ቁጭት ፣ ቁጣ መገለጫቸው ይሆናል ። ስሜቶች ቁጥጥር ከሌለው ሌሎች ሰዎችን ሳያውቁት ሊጎዱ ይችላሉ ። 5- ድንጉጥ እና ደንታ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ ። ቶሎ ይቆጣሉ ፣ ሁሉንም ነገር በነቂስ ይከታተላሉ ፣ ይበረግጋሉ ፣ ይወራጫሉም ። እንቅልፍ ላይ ይሰቃያሉ ፣ በህይወታቸውም ደንታ ቢስ ይሆናሉ ። ህክምናው የስነልቦና እንዲሁም የመድሃኒት ናቸው ። ጊዜ የሚፈልግ እና ቀስ በቀስ በሂደት የሚስተካከል የህመም አይነት ስለሆነ በጊዜ ከታከመ ዉጤታማነቱ አመርቂ ይሆናል ። ቸር እንሰንብት ምንጭ ( DSM 5 )
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 21