አጃዒብ
ማቃጠላቸውም አይደለም አስገራሚው ነገር ። አመዱን ሰብስቦ በማንሳት ከውስኪ ጋር ቀላቅለው ግጥም አድርገው መጠጣታቸው እንጂ ። ያለፈውን መጥፎ ትዝታ ፍቆ መጪውን ብሩህ ያደርገወ ዘንድ የሰው ልጆች የሁሉም ግዜ ተስፋ ነው ። አዲስ አመት ሲመጣ ደግሞ ይህ ስሜት ገዝፎ ልምድና ባህልን ወለደ ። ይህም ብዙ አስደናቂ እምነቶችን እንዲፈጥር አደረገው ። እናም ምኞት ያሰከረው የሰው ልጆች የአዲስ አመት አከባበር እንዲህ ባሉ አጃኢበተኛ ድርጊቶች የታጀበ ሆኗል ነው የዚህ እትም የአጃኢብ አምዳችን ተረኩ ። ታዲያ እንደ ኢትዮጵያዊ ቀጣዩ አመት መልካም ይሆን ዘንድ እሪሪ ብሎ መጮህ ወይም እቃ መስበር አልያም አመድ በውስኪ መጨለጥ አያስፈልገንም ። ከየፈጥሮ ጋር የተናበበ በውበትና ስነ ስርዐት ያማረ ውብና የሚያኮራ የመልካም ምኞት መግለጫ ባህል አለን ። ምርቃቱ ቄጤማው አበባውና ፀሎቱ ሁሉ ! ይህን ጠብቆ ማቆየት ይገባናል ። አንባቢያን ሆይ አዲሱ አመት ከመመኘት ወደ ማግኘት የምንለወጥበት ፤ እንደ አደይ ህልማችን የሚፈካበት ፤ እንደሳሩ ተስፋችን የሚለመልምበት ፤ እንደ መሬቱ አረሙ ከስሞ ፍሬው የሚያብብበት ይሁንልን ። ስደተኛው ለቤቱ ቤተኛውን ለክብር ያብቃልን ። ፍቅራችንን መከባበር ፤ መከባበራችን መተላለፍን ይውለድልን ። በቅንነታችን በበጓነታችን እና ለሀገር ወዳድነታችን የሚሆን ሰፊ ልቦና ያለምልምልን ። ሰናይ አዲስ ዘመን !
ቅንድል
ይደውሉልን ! 0912178520
0920019699
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 17