ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 18

ቅምሻ ዶ / ር እዮብ ማሞ again

ቅምሻ ዶ / ር እዮብ ማሞ again

እንደገና እንዳትሳሳቱ . . .

እንደ አዋቂዎቹ ግምት ከጥቃቅኖቹ አንስቶ ወሳኝ የሆኑትን ጨምሮ በየቀኑ ከሰላሳ አምስት ሺህ ያላነሱ ውሳኔዎችን አስበንና አሰላስለን እንወስናለን ይባላል ፡፡ አስቡት ! በ2013 ባሳለፍናቸው 365 ቀናት ውስጥ አናሳዎቹንና አንጋፋዎቹን ጨማምሮ በድምሩ ከ12 ሚልየን በላይ ውሳኔዎችን አድርገናል ማለት ነው ( ለማመን ቢያስችግርም )፡፡
ቁጥሩ በዛም አነሰም የከትናንት ወዲያ ውሳኔያችንን ትናንት ኖረን አልፈናል ፤ የትናንትናውን ውሳኔ ደግሞ ዛሬ እየኖርነው ነው ፡፡ ስለሆነም የነገውን ኑሮ ለመቀየር ካስፈለገ የዛሬን ውሳኔ በሚገባ ማጤን አስፈላጊ ነው ፡፡
አንዳንዶቻችን በ2013 ዓ / ም የወሰንናቸው ውሳኔዎች ውጤትም ሆነ መዘዝ አብሮን ወደ 2014 ይሻገራል ፡፡ ያለፈው ስላለፈ ፣ እንዲሁ ከመጸጸት ይልቅ መጪውን እንዴት እንደምናደርገው በሚገባ ማሰብ ይበጃል ፡፡
ስሌቱ አጭርና ግልጽ ነው ፡፡ የተዛባ ውሳኔ የተዛባ ሕይወት ! ይህ ስሌት የእናንተን ሁኔታ የሚጠቁም ከሆነ ልክ አንደ 2013ቱ ይህ እንዳይሆን ከፈለጋችሁ ሶስት እርምጃዎች ያስፈልጓችኋል ፡፡
1 . ማንኛውንም ውሳኔ ከመወሰናችሁ በፊት ውሳኔያችሁ ከዋናው የሕይወት ዓላማና ከዋና ዋናዎቹ የሕይወት እሴቶቻችሁ ጋር መጣጣሙን እርግጠኞ ሁኑ ፡፡
2 . ማንኛውንም ውሳኔ ከመወሰናችሁ በፊት በሚገባ ለማሰብ በቂ ጊዜ መውሰዳችሁን እርግጠኞች ሁኑ ፡፡
በ2013 ዓ / ም ደጋግማችሁ ያደረጋችኋቸውን ነገሮች መለስ ብላችሁ ብትመለከቱ በዚያው ዓመት ያዳበራችኋቸውን ልማዶች ያመለክቷችኋል ፡ ፡ አንዴ የተደረገ ተግባር የመደገሙ እድል የሰፋ ነው ፡፡ ስለዚህ አንድን ተገቢ ያልሆነ ተግባር ቀድሞውኑ አለመጀመር ይሻላል ፡ ፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የተደጋገመ ተግባር ወደ ልማድ የመቀየሩ እድል የጎላ ነው ፡፡ ስለዚህ አንዴ ያደረግነው ነገር ጤና-ቢስ እንደሆነ እንዳሰብም ላለመድገም መጋደል የግድ ነው ፡፡
አንድ ጊዜ ከጀመርነው በኋላ ብንደጋግመው ምንም ችግር እንደሌለበት አስበን የደጋገምነውና ወደ ልማድ የተቀየረው ነገር የሕይወትን አቅጣጫና ፍጻሜ የመለወጥ አቅም ይህ ነው አይባልም ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያቱ የምናዳብራቸው ልማዶች ሕይወትን አስረው የማስቀረት ጉልበት ስላላቸው ነው ፡፡
ሕይወታችሁ መታሰሩን ማወቅ ከፈለጋችሁ ቀላሉ መንገድ የሚከተሉትን ጠቋሚዎች ማየት ነው ፡ ፡ ቀድሞ በጉጉት ታደረጓቸው የነበሩ መልካም ነገሮችን ካቆማችሁ ፣ ውስጣችሁ ያለው አቅም ትልቅ ፣ የምታከናውኑት ነገር ግን ትንሽ መሆኑን ካያችሁ ፣ ከጊዜ ወደጊዜ ከማደግ ይልቅ እዚያው ከረገጣችሁ ወይም ወደኋላ ከቀራችሁ . . . በአጉል ልማድ ታስራችሁ ይሆናልና ሁኔታውን አጢኑት ፡፡
ሶስት ጥያቄዎች ይመለሱ . . . 1 . በ2013 ዓ / ም የጀመርኩትና በ2014 ዓ / ም የግድ ማቆም ያለብኝ አጉል ልማድ ምንድ ነው ?
2 . በ2014 ዓ / ም አጉል ልማድ ከማዳበር ይልቅ 3 . ማንኛውንም ውሳኔ ከመወሰናችሁ በፊት
ጠቃሚ ልማዶችን ለማዳበር እንድችል ምን ምን ( በተለይም ጠንከር ያሉትን ) በልምምድና
አይነት የሕይወት ዘይቤ ለውጥ ማድረግ ይኖብኛል ?
በጥበብ ከእናንተ ቀደም ያሉ ሰዎችን አማክሩ ፡፡
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 18