አናናስ ግርማይ
የሥነ-ማህበረሰብ ባለሙያ britanitam @ gmail . com >
ማን ነው ? አትችይም ያለሽ ?
ንንሳ አወት
የፆታ እኩልነት ሰብአዊ መብት ቢሆንም በአለም ያሉ ሴቶች በኢኮኖሚ ተሳትፎ ፤ መሰረታዊና ከፍተኛ የትምህርት እድል ፤ የፖለቲካ ውክልና ፤ ጥሩ የጤና አገልግሎት እና ከአደጋ ጥበቃ በማግኘት በኩል ከወንዶች እጅግ ያነሰ እንደሆነ ብዙ ጥናቶች የሳያሉ ፡፡ የሴቶች መብትን ማክበርና በውስጣቸው ያለውን አቅም ማውጣት እንዲችሉ እኩል እድል ማግኘት የሚስፈልጋቸው የፆታ እኩልነት ለማምጣት ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ የልማት ግብን ለመምታት ይጠቅማል ፡፡
በኢትዮጵያ ከጠቅላላ ህዝብ 80 % በገጠሩ ክፍል የሚኖረው ሲሆን አብላጫውን የግብርና ጉልበት የሴቶች ቢሆንም ምንም አይነት እውቅና ስለማይሰጠው ግብአቶቹ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ሁሉ በአባት ወይም በባል ቁጥጥር ስር ይውላል ፡ ፡ ከሦስት ሴቶች አንድዋ አካላዊ ፤ ስነልቦናዊና የወሲብ ጥቃት ይደርስባታል ፤ 65 % ሴቶች ግርዛት ያስተናግዳሉ ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ት / ቤት ከገቡ ሴት ህፃናት ውስጥ ግማሹ ብቻ 5ኛ ክፍል መድረስ ይችላሉ ፡፡ ( Gender Equality and Women Empowerment / Ethiopia / USAID-2020 ).
ወደ ርዕሴ ስመጣ ከላይ ያሰቀመጥኩት እውነታ በሴቶች እለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነ ግልፅ ነው ፡፡ ሆኖም ግን ይህን ከባድ ጫና ተቋቁመው እና እኩል እድል መጠቀም እንዲችሉና ወደ ( Equty ) እንዲመጡ ቢደረግ ከውንድም በላይ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ያሳዩ በርካታ ሴቶች አሉ ፤ ይህም የይቻላል ስሜትን ይፈጥራል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የፆታ እኩልነት እንዲመጣ በሰፊው እንቅስቃሴ እየተደረገ ቢሆንም ሴቶች ተወዳዳሪ ሆነው በከፍተኛ ባለሞያነት ፤ በኢኮኖሚውና እና በፖሊቲካው ያላቸው ተሳትፎ ካላቸው ቁጥር ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አደለም ፡፡ እዚህ ላይ ከላይ ያስቀመጥኩት ችግር እንዳለ ሆኖ ሴቶች በቤተሰብ ደረጃ ከልጅነታቸው ጀምሮ በተለይ በታዳጊነት እድሜያቸው በሰውነታቸው ፤ በስሜታቸው እና በአስተሳሰባቸው ላይ ከፍተኛ
ለውጥ ሲመጣ ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ ጋር በቅርበትና በግልፅነት ለውጦችን እንዴት መቀበል እንዳለባቸው ስለማይወያዩ እና ግንዛቤ ስለማይሰጣቸው በዚህ ከባድ የእድሜ ክልል ላይ ለሚገጥሟቸው ጉዳዮች ሁሉ ከነሱ ጋር ተመሳሳይ በሆነ የእድሜ ክልል ላይ እና የግንዛቤ መጠን ካሉ ጓዶቻቸው ጋር ብቻ በመወያየት ጊዚያዊ ስሜታቸውንና ፍላጎታቸውን የሚያረካ ውሳኔ በመወሰን ወደፊት ሊሆኑ ያለሙትን ግብ ሳያዩ በአጭር ሲቀጩ የምናያቸው ሴቶች በርካታ ናቸው ፡ ፡ ታዲያ በዙርያቸው ያለው ማህበረሰብ ደግሞ የኛ ሚና ምን ነበር ብሎ ሳይሆን የሚጠይቀው የተለመደውን አባባል አይ የሴት ነግር በማለት ተስፋ አስቆራጭ የሆነ አስተያየት ከመስጠት ውጪ አስተማሪ የሆነ ግብዓት ሲሰጥ አይታይም ፡፡
እኔ ግን አጥብቄ መከራከር የምፈልገው ምንም አንኳን ሴት በመሆንዋ ሊገጥማት የሚችትለው ነገር ብዙ ቢሆንም ከፊትዋ የሚገጥሟት መሰናክሎች መውጣት የምትችለው የራስዋ የሆነ ርእይ እና የህይወት ተልዕኮ ሲኖራት ነው ፡፡ አንድ ሴት መሆን የምትፈልገውን ነገር ዛሬ ላይ ሆና ማየት ( ማለም ) ከቻለች በየዕለቱ የሚገጥምዋት ነገሮች ሁሉ ወደ ፈለገችው ቦታ ለማድረስ የሚያግዙ ናቸው ወይስ እንዳትደርስ የሚያሰናክሉ ናቸው እሚለውን መለየት ያስችላታል ፡፡ Sean Covey : The Seven Habit of Highly Effective Teen በሚለው መፅሃፈቸው እንዳስቀመጡት ( Proactive People ) በአመክንዮ መልስ የሚሰጡ ሰዎች እለት እለት በነሱ ላይ የሚፈጠር ነገር ሁሉ መቆጣጠር እንደማይቸሉ ተገንዝበው እያንዳንዱን ሁኔታ ወይም ተግዳሮት ምን አድርግው በቁጥጥር ስራ ማዋል እንዳለባቸው ያውቃሉ ይላሉ ፡፡ እኔም ፅሁፌን ሳገባድድ በሴትነታችን ሊገጥሙን የሚችሉ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም ርእያችን እውን እንዳይሆን የማድረግ ጉልበት የምንሰጣቸው አልችልም በማለት የራስን አቅም ባለማወቅና ባለማሳድግ የምንፈጥረው የአስተሳሰብ ዉስንነት ዉጤት በመሆኑ ልንታገለዉና በአሸናፊነት ልንወጣዉ ግድ ይለናል ፡፡
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 15