ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 9
እንዲያውም „ተራው ከእንግዲህ የእኛ ነው!“ የሚለውን ቃል አብረው
ለቀው „አርፋችሁ ተቀመጡ አለበለዚያ…“ የሚለውን ማስፈራሪያ
አክለውበት በግዛታቸው የሚገኙትን ኃይሎች ጸጥ ለጥ አድርገዋል።
1
ቀደም ሲል እንደምናውቀው „እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም“ የሚለውን
ቅስቀሳም አካሂደው አባሎችም ደጋፊዎችም ሰብሰበዋል።
በዘመኑ ተጽፎ እንደተነበበው „…የትግራይ ትግርኛ መንግሥት“ በሰሜን
ምሥራቅ አፍሪካ „የኦሮሞ ሪፓብሊክ“ ደግሞ እነደዚሁ ከኢትዮጵያ
ተገንጥላ/ተገንጥለው በዚያ አካባቢ እነዚህ ድርጅቶች ለማቋቋም
አቅደው አንደነበር በጽሑፍ ላይ ቀርቦአል በየአለበት ተነቦአል።
ለአረቡና ለቱርኩ ለሕንዱና ለቻይናው በሦስተኛ ደረጃ …ማንም ከየት
መጥቶ የእርሻ መሬቱዋን በትንሽ ገንዘብ ለሚመጡት አርባና ሃምሳ
ስድሳ አመታት …አልፎም ያሄዳል የሚገዛት አገር ናት።
ዛሬ መሬቱዋን ነገ ብሔራዊ ሕልውናዋን …ከነገ ወዲያ ደግሞ ሕዝቡዋን
እንገዛለን ልንገዛ እንችላለን ባዮች ጥቂት አይደሉም።
አንግዲህ ይህች የፈረደባት ኢትዮጵያ የማን ናት?
2
እናት አገርን መክዳት አዲስ ነገር አይደለም። የትም ቦታ ያለ እና
የሚታይ ነገር ነው። ግን ቁጥራቸው ብዙ ሳይሆን ይህን የሚያደርጉ
እንደዚህ የሚያስቡ ሰዎች በታሪክ ላይ ብዙ ቦታ ተደጋግሞ ታይቶአል።
ቁጥራቸው ግን ቢቆጠሩ በጣም ጥቂት ናቸው።
እንደ ኢትዮጵያ ግን ቅጥ ያጣ ቦታና አገር የለም።
ጌጥ ሁኖ አንዱ ወገን ሌላውን ለመብለጥ የማይልውና የማያደርግረ ነገር
የለም።
9