ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 8
ሁለት ወገኖች እናያለን። ለአንደኛው „ኢትዮጵያ“ የግል ሐብቱ ናት።
እንደምናየው እሱም እንደፈለገው በቃላትም በገንዘብም እንደ ግል
ንብረቱ „…ይሸጣታል። ይለውጣታል።“
ለሁለተኛው -እሱ ስለ ከዳት- ብትኖር ብትጠፋም እንደምናነበው
ቅንጣት ያህል እንኳን ግድ የለውም።
እንደ ምንም ብሎ በዚያም በዚህም አድረጎ ድል አድረጎ ቤተ-መንግሥት
ለገባው ሰው ሁሉ ይህች አገር እዚያም ምድር ላይ የሚኖር ሰው ሁሉ
„የግል“ ሐብቱ ነውና ቢፈልግ ከመሬቱ ሊነቅለው ይችላል።
ሊያባረውም።ሊያስረውም ። ሊቀጣውና ተደጋግሞ በተለያዩ ዘመናት
እንደታየው ሊገድለውም ይችላል።
ደርግ እንደዚህ አድርጎ ነው በግዛት ዘመኑ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን
ሕዝብ ያኔ ያየው።
እህአዴግ ሻብዕያና ለጥቂት ጊዜያቶች አብሮ ከሁለቱ ጋር ለሠራው ኦነግ
– ድል አድራጊ እነሱ በዘመናቸው ስለነበሩ- „ሁሉም ነገር“ ጊዜውም
ዘመኑም ንብረቱም የኛ ነው ብለው የመጀመሪያው አመታት ላይ እነሱ
እራሳቸው እንደጻፉት እስከመተናነቅ ድረስ ሄደዋል። ።
ድሮ
8