ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 10
„ተማሩ“ ከሚባሉት ሰዎች መካከል ቁጥራቸው „ከፍ“ ያለ ወገን በእናት
አገሩ በኢትዮጵያ ላይ አድሞ እሱ የሚሰነዝረውን አስተያየቱን ማዳመጡ
የትም ያልታየ የትም ያልተሰማ በጣም የሚገርም አዲስ ነገር ነው።
በታሪካችን ጦር መዘው ከጠላት ጋር ቆመው ይህቺን አገር የወጉ ሰዎች
አሉ። መጥላት ብቻ ሳይሆን እንድትጠፋም የሚፈልጉ ሰዎችን አገሪቱ ይህ የትም ያለ ነው- አፍርታለች።
„የምኒልክ ኢትዮጵያ ትሙት… „ ብለው እኛ ጋ እንደሚፈርሙት ዓይነት
ሰዎች ሌላም አካባቢም ታሪክ ላይ እንደአነበብነው የትም በቅለዋል።
የኢትዮጵያው ግን ይብሳል። ከሁሉም ይበልጣል።
ለምን እንደዚህ ሆኑ?
ለምን እነደዚህ ጨከኑ? ለምን አገራቸውን ጠሉ? ባለማወቅ ይሆን
ወይስ አውቀው የሚያደርጉት ነገር ነው? ፕሬዚዳንቱዋ የነበሩት ሰው
ከእሳቸው አፍ የሚሰማው ያስገርማል። አገረ ገዢዎቹ የሚሉትን ስንሰማ
ያስደነግጣል።
ዛሬ
3
ኢትዮጵያ የማን ናት? ብሎ መጠየቅ አሜሪካን የማን ናት? ብሎ
እንደመጠየቅ ነው። …ፈረንሣይስ የማን ናት? ታላቁዋ ብርታኒያስ?
10