ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 11
ቻይናስ? ኬንያስ? ሕንድስ የማን ናት? ብሎም ጠይቆ መልስ
እንደመፈለግ ዓይነት ነው።
ኢትዮጵያ የኢትዮጵያኖች አገር ናት። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ
የሚያምን ሰው ሁሉ አገር ናት።
አሜሪካ አገር ሄደው የሚወልዱትንም ዘመዶቻችን መረዳት የምንችለው
ይህን ስንገነዘብ ነው። እዚያ የተወለደ ልጅ እዚያ ዜግነቱን የተቀበለ ሰው
እሱ „ ሙሉ አሜሪካዊ ሙሉ የአሜሪካ ዜጋ ነው።“
ይህ ሰው ሊመረጥም ሊመርጥም ከፍተኛ የኃላፊነትም ደረጃ ላይ ቀለሙ ዘሩ ሓብቱ ጾታው ሳይታይ- ሊወጣ ይችላል።
ኢትዮጵያ ውስጥም የተወለዱ አርመኖችና ጣሊያኖች ግሪኮችና አረቦች
ሱዳንና
ግብጾች
ሕንዶችና…(
አሁን
ደግሞ
ቻይናዎች(?)ተጨምረውበታል) እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ ዜግነት
ያላቸው ሰዎች ናቸው።
ማለት በሕግ በታወቀው ግዛቱዋ ያኔ/አሁንም የተወለደ ሰው ሁሉ
(የዛሬውን አናውቅም) የአገሪቱ ዜጎች ናቸው።
ግን ደግሞ በዚያው መጠን „እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም „ የሚለውን
ሰው -ይህን ለማለት መብቱ ነው- በግዳጅ ኢትዮጵያዊ ማድረግ
አይቻልም።
ይህ ከሆነ ደግሞ „ኢትዮጵያዊነቱን“ ከማይቀበል ሰው ጋር ጥዋት ማታ
መነታረኩ ከንቱ ነው።
„እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም „ ብሎ „በኢትዮጵያዊነቱ ለመደራደር…“
ከሚፈልግ ሰውና ድርጅት/ድርጅቶች ጋር ምን ማድርግ ይቻላል?
ስለምን መደራደር እነሱ እንደሚሉት ይቻላል? ማን በማን ስምና ሌጋሲ
ድርድሩን ሊያካሄድ ይችላል? ምን ላይ ተመስርቶስ መነጋገር ይቻላል?
4
እንደዚህ ዓይነቱን „ችግር“ ሌላው ዓለም በሌላ ብልሃት ነው የፈታው።
11