ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 5
ይህን የምንልበት ምክንያትም አለን።
ሌላው ዓለም እንደ እኛ „በነገር አብዶና ተሳክሮ ተዋግቶና ተጨራርሾ
በመጨረሻው ለስደት ተዳርጎና ተበትኖ ሲንከራተት አልታየም። ይህ በቂ
ማስረጃ ነው።
ምናልባት ሱማሌ ናት። ምናልባት አፍጋኒስታን። ምናልባት ግብጽና
ሞዛቢክ ኮንጎና…እነሱም የተበጣበጡት – መለስ ብሎ ታሪክን
መመልከትን ይጠይቃል – በዚሁ አፍሪካና እሲያ ቀስ ብሎ ሰተት ብሎ
በገባው „ የተለያዩ ትምህርቶችና በእነሱም ፍልስፍና “ነው። ከዚያም
ለመውጣት በሚያደርጉት መፍጨርጨር መንገዱ ጠፍቶአቸዋል ።
የሚደንቀው እኛ ሁኔታ ነው። እኛ ገና „…ዲሞክራሲ በገደብ፣ የለም
ዲሞክራሲ ያለ-ገደብ፣ ዲሞክራሲ ለሁሉም፣ የለም ዲሞክራሲ ለጭቁኑ…
ከነአካቴው ገና አርባ አመት ጠብቅ „ ስንባባል፤ የሞራል ፍልስፍናን
መሠረት አድርገው „ለጋማና ለቀንድ ከብት ለለማዳ ውሾችና ለሰለጠኑ
ድመቶች…ሙሉ የዜግነት መብት ይሰጣቸው“ የሚሉ ጸሓፊዎችና
ፈላስፋዎች እዚህ አውሮፓና እዚያ አሜሪካ ብቅ ማለታቸውና
መነሳታቸው ደግሞ እጅግ አስደስቶናል።
ይባስ ብለው አንዳንዶቹማ „ …ለቀበሮና ለተኩላ ለርግብና ለአሞራም
የመኖር መብታቸው ተከብሮ ተጠብቆ በእኩል ዓይን እንደ ጎረቤት ዜጋ
ከእንግዲህ እንዲታዩ „ -ይህ አንጀት ያርሣል – እሰከ መጠየቅ ድረስ
ዘልቀዋል።
እኛም ይህን ጉዳይ እንድታዩት የአነሳነው የሰው ልጆች
በአስተሳሰባቸውና በአመለካከታቸው የትና የት -እኛ እዚያው ነገር
ውስጥ ስንዳክርና ስንከባለል- ጥለውን እንደሄዱ ለማሳየት ብቻ ነው።
ተመልከቱአቸው አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮች ስለ ተረሳው ስለ ሞራልና ስለ
ኤትክ ፍልስፍናዎች ታገኙበታላችሁ።
እኛም ደግሞ፤…. ስለ አንድ በዓለም ታሪክ ስለሚታወቅ ከሰጎን
የሚበልጥ ግርማ ሞገስ ስለ አለው ግሩም “የኢትዮጵያ” ትልቅ አሞራ፣
„የማታውቁት እንድታውቁ“ የምታውቁም እንድታስቡበት፣ ስለ እሱ
የሕይወት ታሪክ በጥቂቱ አንስተናል።
5