ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 4
አንዳንድ ግንዛቤ (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial)
Published February 28, 2014 አንዳንድ ግንዛቤ (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial)|
አንዳንድ ግንዛቤ (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial)
እንደ ጀመርነው በየወሩ አንዳንድ ጉዳዮችን- ውድ አንባቢ- እናነሳለን።
ዛሬም እንደገና ኢትዮጵያ የማን ናት? ብለን እናንተንም እንጠይቃልን።
ዩናይትድ እስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሆነች ወይም ፈረንሣይ ወይም ደግሞ
ደቡብ አፍሪካ የአሸናፊው ፓርቲ „ የግል ንብረትና የግል ሐብት“
እንዳልሆነች ሁላችንም እናውቃለን።
በተቃራኒው ቻይና ወይም ሰሜን ኮሪያ ወይም ደግሞ ኪዩባ የአሸናፊው
ድርጅት ያውም የመሪው ቁንጮ „የግል ንብረት“- እነሱ በቃላት ጨዋታ
„የጭቁኑ ሕዝብ“ ጥዋት ማታ ይበሉ እንጂ-መሆናቸውን በደንብ
ይህንንም ጉዳይ ለይተን እናውቃለን። እንረዳለን።
….ኢትዮጵያ የማን ናት? ኤርትራስ ? ኦሮሞና… አማራስ? የሚለውንም
ጥያቄ የምንሰነዝረው -ዘለቅ ብላችሁ አንደምትመለከቱት- ከዚሁ አንጻር
ነው።
አንዳንዴ ይህ የስታሊን ቲዎሪና ትምህርት ኢትዮጵያ ባይገባና ባይስፋፋ
ኑሮ ሰው ሳያልቅ ትውልዱ በነገር ሳይሳከር ይህች አገር በሥልጣኔዋ
እንደ ሌሎቹ መንግሥታትና ሕዝብ የትና የት በደረሰች ነበር እንላለን።
… ደርግም ነጻ-አውጪም ጦርነትም ስደትም ክትትልም አምባገነነንትም
አለመደማመጥና አለመግባባትም የሚባለውም ነገር በልጆቹዋ መካከል
ፈጽሞ በአልተፈጠረም ነበር ብለን እንገምታለን።
4