Test Drive April 2015 | Page 9

እንደሚጓዝ ፊጋ በሬ የመኪናውን ጥሩንባ እያስጓራ የሚሮጥ መኪና የእግረኛ መንገዱን ያልለቀቁትን መንገደኞች ሲራገምና ሲሳደብ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም ፡፡ ከዚሁ በተጓዳኝ በትራፊክ መጨናነቅ የተነሳ ረጅም ረድፍ ሰርተው ከቆሙት መካከል አፈንግጦ በመውጣት ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጣውን መኪና መንገድ ዘግቶ አላፊ አግዳሚውን አላሳልፍ የሚል የመኪና አሽከርካሪ ከየትኛው ሃገር ወይም ማህበረሰብ የወስድነው ባህል፤ ትውፊት እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል ፡፡ ጊዜያችን ለኔ.. ለኔ.. የሚባልበት ማጭበርበር፤ ማምታታት፤ ጉቦኝነት፤ ሸፍጥ፤ ክህደት "ቢዝነስ" የሚል ካባ ደርቦ የሚሞካሽበት፤ የሚሽሞነሞንበት ዘመን ላይ መሆናችን ከጅብ ቆዳ የተሰራ መሰንቆ ቅኝቱ "እንብላው እንብላው" ነው የሚሉትን ተረት ያስታውሰናል ፡፡ ታዲያ መቼ ነው ምነቃው? አንዳንዴ መደንዘዝ አይሉት መተከዝ ታክሲ ለመሳፈር የተለመደውን ረዥም ሰልፍ ከተሰለፉ "ጥቂት" ሰወች አንዱን ሰልፉ የት እንደሆነ ብትጠይቁት የት ለመሄድ እንደተሰለፈ እንኳ የማያውቅ ተሳፋሪ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም ፡፡ ኢትዮጽያዊ ባህሎቻችንና ትውፊቶቻችን ከአውሮፓና ከአሜሪካ በመጡ አደንዛዥ ፕሮግራሞች መጠመዳችን ፤ የኛነታችን መለያ የሆኑትን የአባቶቻችን ተጋድሎ ማራከስና ማንቋሸሽ የወጣቶቻችን መለያ ከሆኑ ሁለት አስርተታትን አስቆጠረዋል ፡፡ ወላጆች ለልጆቻችን ምናወጣው ስም የማንን ባህል እና እምነት እንደሚያንጸባርቅ ከቶ ሊገባን አይችልም ፡፡ ክፉ መንገድ እመልካም ግብ አያደርስም፤ ክፉ ስራ እንደተኮሱት ጥይት አላማውን ይገድላል የሚል አባባል የት ነበር ያነበብኩት ፡፡ ይህንን ማህበራዊ ቀውስ "ጥቂቶች" የነቁ ቢረዱትም የት ወስደው ከማን ጋር ተመካክረው ቅጥ እንደሚያስዙት ግራ ገብቷቸው መቆዘም ብቻ ሆኗል እጣ ፈንታቸው ፡፡ በኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የሚለቀቀው ፕሮግራም ይህንን ማህበራዊ ውጥንቅጥ እና ቀውስ ከማስተካከል ይልቅ በእሳት ላይ ቤንዚን የሚያርከፈክፉ ሃይ ባይ የሌላቸው ሚዲያዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል ፡፡ "ጥቂቶችን" እንደሆነ ልብ ይባልልኝ ግን፤ ግን መቼ ነው ʼምነቃው ብለን ማጠየቃችን አልቀረም ፡፡ ጥሪታችንን አሟጠን በእውቀት ሰጪነቱ፤ በገንዘብ ተቀባይነቱ አንቱ የተባለ ት/ቤት እውቀት እንዲገበዩ የላክናቸው ልጆቻችን ነገ የሀገር ተረካቢ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ያሰብን "ጥቂት" ወላጆች ልጆቻችን ስልጣኔ ምልክት ተደረጎ በሚወሰደው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ልክፍት በያዛቸው "ጥቂት" ት/ቤቶች አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር የተከለከለ ነው በማለት ህግና ስርዓት ሲያወጡ ስንመለከት እውነት ያለነው እምዬ ኢትዮÉያ ውስጥ ነው ወይስ .. ብለን መደናገራችን አይቀርም ፡፡ ሳስበው፤ ሳስበው እነዚህ "ጥቂት" ሰወች ቀኝ አለመገዛታችን የእግር እሳት ሳይሆንባቸው አልቀረም ፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በትምህርት ቤት ያለው የተማሪና የአስተማሪ የመከባበር ስነ-ምግባር ከተናደ እንዲሁ ... አስርታትን አስቆጥሯል ፡፡ እነዚህ ተቋማት በእውቀት አንጸውና ኮትኩተው የሚያፈሩት ትውልድ ሀገር በሁለት እግሩ እንዲቆም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወሰድ ይታወቅ ነበር ፡፡ ነበር ፡፡ በአንድ ወቅት አያችሁ የጄኔሬሽን ዝቅጠት አለብን ያሉ ሰው አስታውሳለሁ ፡፡ በዛሬውና በርሳቸው ጊዜ የነበረው የጄኔሬሽን ዝቅጠት ሚዛን የትኛው ውሃ ያነሳ ይሆን ፡፡ ከዝቅጠትስ በታች ቋንቋ ይኖር ይሆን ?ታዲያ መቼ ነው ʼምነቃው? የእነዚህ እና የሌሎች ማህበራዊ ህፀፆቻችን ድምር ውጤት ነው የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናችንን የሚያጎለብተው ፡፡ ጥቃቅን ሚመስሉን ነገር ግን በጥቅሉ ሲታዩ ማህበራዊ እሴቶቻችንን የሚጎዱ ድርጊቶች ናቸው ነቅተዋል አልነቁም የሚያሰኙን ፡፡ ሰድበው ለተሳዳቢ የሚሰጡን ፡፡ ያʼርባ ቀኑን ጉዞ አርባ ዓመት የሚያስጉዙን ፡፡ ትንሽ ፍሳሽ መርከብ ታስመጣለች እንዲል ቤንጃሚን ፍራንክሊን ፡፡ እነሆ ዛሬም 3ሺህ ዘመን ትርክት ላይ ሆነን አልነቃችሁም ገና እያንጎላጃችሁ ነው እየተባልን ነው ፡፡ ጎበዝ አያሳፍርም ? ስንቴ ይሆን የምናፍረው ? በስንቱስ ይሆን የምናፍረው? ለብዙ ኪ.ሜትሮች መነሻው አንድ እርምጃ ነው የሚሉት ቻይናዎች ሃገራችን ገብተው እየሰሩ ነው ከʼነሱ ጋር አንድ ብንል እኮ ነገ....