Test Drive April 2015 | Page 10
የኔ ሃሳብ
አዜብ ዓለማየሁ
እኔ’ምለው
ባህሌን………..ባህሌን…………ያልኩባቸው ቀናቶችና ጊዜያቶች እጅግ
እየበረከቱ ከመጡ ውለው አድረዋል እራሴን ዘውር ብዬ
እንድመለከት ያደረጉኝ ጊዜያቶችም በረከቱ ያ’ገሬ ልጆች… እስቲ
ለሰከንድ ምን ላይ እንዳለን እራሳችንን እንመልከት ውበታችንን፣
ማንነታችንን፣ ባህላችንን፣ ራሳችንን ከረሳነው እና በሌሎች ማንነት
ከተሸፈንን ሰንብተን…. የምወዳቸው የአገሬን ልጆች እንድታዘብ
ያደረገኝ እና ይህንን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን በአገራችን
ተካሂዶ በነበረው አንድ የሽልማት ስነ-ስርዓት ነው "ሰው ለሰው"
ድራማ ፡፡ ድራማው በኢብኮ ለ3 ዓመት ተኩል ሲተላለፍ የነበረ
ድራማ ነበር፤ እኔ በዚህ ጽሁፌ ስለድራማው ይዘት ልጠቅስ
አልፈልግም ነገር ግን ተሸላሚዎቹ ለብሰዋቸው የነበሩት አልባሳት
ላይ ያለኝን አስተያየት ለመሰንዘር እንጂ በቀን ተቀን ኑሮችን ውስጥ
የባህል ልብሳችንን እንልበስ ወይም በየዝግጅቱ የባህል ልብስ ግድ
ይለበስ የሚል አቋም የለኝም ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት ትላልቅ
ዝግጅቶች ላይ በተለይ ታዋቂ ሰዎቻችን(አርቲስቶቻችን) የኛ
ኢትዮጵያውያን መገለጫ አገርኛ የሆኑ አልበሳቶችን ለማስተዋወቅ
ከእንደኔ አይነቱ ተራ ሰው የተሻሉ አምባሳደሮች ይመስሉኛል፡፡
በዚህ የሽልማት ዝግጅት ላይ ከሁለት ወይም ከሦስት የማይበልጡ
አርቲስቶች የባህል አልባሳቶቻቸውን የለበሱ ቢሆንም አብዛኛኞቹ
ግን እጅግ አጫጭር ቀሚሶችንና ለዝግጅቱ ሊመጥኑ የማይችሉ
አልባሳትን ነበር ምርጫ ያደረጉት ሌላው ቢቀር እድሜን እንኳን
ያላገናዘበ አለባበስ የለበሱ አርቲስቶችን ተመልክቼ ነበር፡፡ እንደ’ነዚህ
ዓይነት ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የመታየት እድላቸው እጅጉን
የጎላ ነው፡፡ ስለዚህም እንዳ’ባቶቻችን እንደ አያት ቅም-አያቶቻችን
ብሂል "ባ’ንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" እንዲሉ ለብሰነው ብንታይ
ድምቀትና ውበት ፣ ግርማ ሞገስና ጌጥ የሚሰጠን ኩራቻችን
ከዚየም አልፎ መደምቂያችን የሚሆን አገርኛ አልባሳታችን በሆነ
ነበር ፡፡ እናም ታዋቂ ሰዎቻችን እኔ እናተን ልመክር ባልዳዳም
እንደው እንደ እስተያየት እንድታስቡበት ለማለት ያህል ነው፡፡
ሌላው አገርኛ ያልሆኑ አሁን አሁን እንደውም ፍፁም ኢትዮጵያዊ
እየመሰሉ ያሉ እና ድንበር ዘለል የሆኑ ክብረ በዓላቶች እየበዙና
እየሰፉ ከመጡ አመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ምን እየሆነ እንደመጣ
ለመገመት ቢከብደኝም ሁላችንም ራሳችንን ለማጠየቅ ባህል፣ ወግ፣
ቅርስ፣ ማንነት የሚባሉት ኢትዮጵያን፤ ኢትዮጵያ ህዝቦቿንም
ሉዓላዊ ያስባሉት ትውፊቶች በአሁኑ ሰዓት ፈፅሞ እየተረሱና እየጠፉ
ለመሆኑ ምስክር መጥራት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡
ሌላው ቢቀር እኔ አገሬን እወዳታለሁ፣ እኔ ሐበሻ ነኝ፣ ኢትዮጵያዊነቴ
ኩራቴ ነው ብሎ መናገር እንደ ኋላ ቀር እና አላዋቂነት እየተቆጠረ
ያለበት ጊዜ ላይ ቆመን እንገኛለን ፡፡
ቫላንታይንስ ደይ፣ ክሬዚ ደይ፣ አፕሬል ዘ ፉል ደይ፣ ክሬስማስ
ደይ……..ወዘተ እየተባሉ ሙሉ በሙሉ ከእኛ ባህልና ወግ የወጡ
ማንነታችንን ፍፁም በሚያጎድፉ አጓጉል በዓላት ውስጥ ተዘፍቀን
እንገኛለን፡፡ አንድ ነገር ላውራ…. የገና በዓልን እናስታውስ
በእያንዳዳችን ስልክ ላይ ከቴሌም ሆነ የቅርብ ጓደኞቻችን የሚደርሰን
አጭር የፁሁፍ መልክትን እናስተውለው… ከጥቂቶች በስተቀር
(Merry x-mass, happy x-mass) የሚሉ መልዕክቶች ናቸው
በእውነቱ ግን እኛን መልካም የገና በዓል የሚለው ነው ሊገልጸው
የሚችለው? ወይስ x-mass የሚለው የፈረንጅ አፍ መልሱን ሁሉም
በልቦናው ይያዘው ማንነታችንን ሊገልጽን የማይችል የገና ዛፍና ባዶ
ካርቶኖችን በስጦታ ወረቀት አሸብርቀን ቤታችንን አድምቀን በዓል
ለማክበር እንታትራለን ፤ ስለ እውነት ነው የምለው እኔ ትርጓሜው
እንኳ አይገባኝም፡፡ የገና ጨዋታን በዓለም አቀፍ ደርጃ ማስተዋወቅ
ስንችል እኛ ግን ስለ ገና ጨዋታ ማውራት የማንችንል ትውልዶች
ሆነናል ፡፡
ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ 365 ቀን የፍቅር ቀን ነው ብዬ አስባለሁ
ፍቅር ከሁሉ ይበልጣልና ታድያ ለዚህ ከሁሉ ይበልጣል ለተባለው
ፍቅር በአመት አንድ ቀን ሰጥቶ ማክበር አያሳፍርም፡፡ በው’ኑ ለኛ
ቫላንታይን ይመጥነን ነበር ? በርግጥ ቄስ ቫላንታይንን
አከብራቸዋለሁ መልካም ቄስም ነበሩ፣ መልካም ስራ ሰርተው
ያለፉ…እኚ ቄስ ለጥቂት ጥንዶች ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ አባት
ናቸው…. አያችሁ እኚ ፈረንጆች ብልጦች ናቸው በስማቸው ቀን
ሰይመው ዓለም እንዲዘክራቸው አደ