Test Drive April 2015 | Page 11

ገጽ ለገጽ ኤስ ኦ ኤስ አለም ዓቀፍ የህጻናት መንደሮች በኢትዮÉያ በዝግጅት ክፍሉ በዚህ አጭር ጽሁፍ ኤሰ ኦ ኤስ በአትዮጽያ ያሳለፈውን 40 ዓመት መዳሰስ እጅግ በጣም ከባድ ነው ፡፡ ይሁንና ከአቶ ወርቅነህ ንጉሴ የኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ዲን ከተምሳሌት ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ ለአንባቢ በሚመች መልኩ ቀንጨብ አድረገን አቅርበነዋል ፡፡ ወደፊት የኮሌጁን አጠቃላይ የትምህርት አሰጣጥ እንዲሁም ተደራሽነት በስፋት የምንመለስበት መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለአንባቢዎቻችን ለመግለጽ እንወዳለን ፡፡ አቶ ወርቅነህ ንጉሴ የኤሰ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን የኤሰ ኦ ኤስ ዓለም አቀፍ የህጻናት መንደሮች ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን የዛሬ 60 ዓመት በ1949 ዓ.ም (እ.አ.አ) በፕሮፌሰር ኸርማን ሜየር በተባሉ ግለሰብ በኦስትሪያ ተመሰረተ ፡፡ ወቅቱም 2ኛ የዓለም ጦርነት ማብቂያ እንደመሆኑ በጊዜው በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ህይወት በመጥፋቱ ምክንያት የብዙ ቤተሰቦች እና ዘመዳሞች አድራሻ በመጥፋቱ ግለሰቡ በዚህ አስከፊ ወቅት የተጎዱትን በመደገፍ እና የተጠፋፉትን በማገናኘት የራሳቸውን አስተዋጽዎ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ ተቋም ነበር ፡፡ ይህንን መሰረት አድርጎ የተቋቋመው ኤስ ኦ ኤስ የስራ አድማሱን በማስፋት በአሁኑ ወቅት ሃገራችንን ጨምሮ በ134 አገሮች ላይ እየሰራ ይገኛል ፡፡ በቅርቡ ፋይናንሻል ታይምስ /Finnancial Times/ በተባለ ታዋቂ የፕሬስ ድርጅት በተደረገ ጥናት ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአቅም እና በበጎ አድራጎት 33ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ኤስ ኦ ኤስ በኢትዮጽያ የዛሬ 40 ዓመት በ1974 ዓ.ም (እ.አ.አ) በሃገራችን ተከስቶ በነበረው ድርቅ በተለይም በትግራይ ክልል የነበረውን ችግር ለመፍታት በክልሉ ተቋቋመ፡፡ በወቅቱ የተከሰተውን ጊዜያዊ ችግር ለመታደግ ይመስረት እንጂ የስራ አድማሱን በማስፋት ላለፉት 40 ዓመታት የተለያዩ በጎ ስራዎችን በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ሰርቷል እየሰራም ይገኛል ፡፡ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጽያ በሦስት ዋና ዋና ተግባሮች መሰማራቱን የገለጹልን አቶ ወርቅነህ ንጉሴ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጁ ዲን እነዚህም ትምህርት፤ ጤና እና የህጻናት እንክብካቤ ናቸው ፡፡ አያይዘውም ድርጅቱ ይህን አገልግሎት የሚሰጠው በሰባት የሃገሪቱ ክልሎች ሲሆን እነርሱም አዲስ አበባ፤ ሐዋሳ፤ መቀሌ፤ሐረር፤ ባህርዳር፤ ጎዴ እና ጅማ ናቸው ፡፡ ድርጅቱ በዋነኛነት የተነሳለት ዓላማ በተሰብ የሌላቸውን ቤት እና ቤተሰብ (መንደር) እንዲኖራቸው ማድረግ ሲሆን በሃገራችንም ቤተሰባቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ያጡ በሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናትን እንደ ወላጅ በመንከባከብ ለቁም ነገር ማብቃት ነው ፡፡ እነዚህ ህ