Test Drive April 2015 | страница 12
በመምህራን ብቃት፤ በማስተማሪያ ቁሳቁስ አደረጃጀት፤ እንዲሁም
በማስተማሪያ ቦታ ስፋትና ጥራት ብቃት ያለው መሆኑን አስመርቆ
የሚያወጣቸው ወጣቶችም ለሃገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል በማቅረብ
ረገድ ክፍተኛ አስተዋጽዎ እያደረገ መሆኑን ገልጸውልናል ፡፡
የኮሌጁን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት የጨረሱትን ወጣቶች የስራ
ፈጠራን አስተዳደር ትምህርትን እንዲሁም የተለያዩ የማነቃቂያ
/motivational/ ንግግር የሚያደርጉ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን
በከፍተኛ ክፍያ በማስመጣት እና በመጋበዝ ተጨማሪ ስልጠና
ይሰጣል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተወሰኑ ወጣቶችን በማደራጀት
ከመንግስት እና ከገንዘብ ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የተለያዩ
ፕሮጄክቶችን በመንደፍ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ከዚያም
አልፎ ስራ አጥ ወገኖቻቸውን በመቅጠር ድጋፍ እንዲያደርጉ ከፍተኛ
ማበረታቻ ይደረግላቸዋል ፡፡
ኤስ ኦ ኤስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከሌሎች በሃገሪቱ ከሚገኙ
ተመሳሳይ ተቋማት የሚለይባቸው የራሱ ባህሪ እንዳለው የሚገልጹት
ዲኑ በኮሌጁ ተምረው የተመረቁ ወጣቶች ተመልሶ የቤተሰብ ጥገኛ
እንዳይሆኑ ስራ እስከማስያዝ እና ከኮሌጁ ከወጡ በኋላም
በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ እስከመከታተል የሚያደርስ
ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸውልናል ፡፡