Test Drive April 2015 | Page 7

ይችላል፡፡ ይህም ደብዳቤ ከመፃፃፍ ለወላጅም በአካል ትምህርት ቤቱ ድረስ ከመሄድ በፍጥነቱ በቀላልነቱ እንዲሁም በርካሽነቱ የተሻለ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ አንድ ነገር ሊነሳ ይችላል ይህም ይዘታቸውንና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መረጃዎች ከየትኛው ወገን ሊመጣ ስለመቻሉና የመረጃው ደህንነት ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ለነዚህ እንደ መፍትሄ ሊወሰድ የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖውን ብቻ በማሰብ ፋይዳውን ሙሉ ለሙሉ ከማጣት ይልቅ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ የአጠቃቀም ፖሊሲና ዕውቀትን ከባለሙያ ጋር በማቀናጀት በቀላሉ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆን ይቻላል፡፡ ሌላው ሊጠቀስ የሚችለው ልምድ ደግሞ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ተማሪዎች ፎቶ በመቀያየር ይሁን ሀሳብ በመለዋወጥ የበይነ መረብ (internet) የመጠቀም ልምዳቸውን ማዳበራቸው ነው፡፡ ይህ ልምድ ደግሞ ለየትኛውም ስራ ወይም ቢዝነስ በጣም አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን እግረ መንገዳቸውን ወደፊት ለሚኖራቸው የስራ ዘመን ራሳቸውን ብቁ እያደረጉ ይመጣሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ተግባር የማህበራዊ ድረ-ገጾች ተፅዕኖ አዲስ ክስተት የፈጠረው አዲስ የሽያጭ (Marketing) ዘርፍ ነው፡፡ ይህም (social media marketing) የማህበራዊ ድረ-ገጽ ሽያጭ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም መፍጠርና ማደግ በብዙ አገራት የሚገኙ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን የማህበራዊ ድረ-ገጽ ማርኬቲንግ ስትራቴጂ መንደፍ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ በአገራችን ብዙ ድርጅቶች ይህንን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የተማሪዎች ይህ ልምድ ወደ ስራው ዓለም ሲገቡ ጥሩ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ማርኬቲንግ ባለሙያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከወዲሁ ማሰብ ያስፈልጋል ፡፡ ወይም በቀላሉ በዚህ ዘርፍ ላይ መሰማራት ይችላሉ ለማለት ይስችላል፡፡ በተለያዩ አገራት የሚገኙ መምህራንም በሚያስተምሩት ትምህርት ዓይነት ስም ማህበራዊ ድረ-ገጽ በመክፈት የቤት ስራን አንኳን በተለያዩ