Test Drive April 2015 | Page 6

ቴክኖ-እመርታ ፌስ ቡክ(face book) ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎች 1.15 ቢሊዮን እንደሚሆንም ታውቋል፡፡ ዓለማየሁ ስሜነህ ማህበራዊ ድረ-ገጾችና ትምርታዊ ፋይዳቸው፡፡ አገራችን በዓለም ላይ ከሚገኙ ዝቅተኛ የኢንተርኔት(የበይነ መረብ) ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበይነ መረብ ፍጥነትና ተደራሽነት ከምንግዜውም በተሻለ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ከሁሉም በተሻለ መጠን የበይነ መረብ አንዱ አካል የሆነው የማህበራዊ ድረ-ገጽና የመወያያ መድረኮች (chat forum) ግን በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቅላላ ጠቀሜታ እጅግ ብዙ እና ዘርዝረን የማንጨርሰው ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳዶች ዘንድ ለወጣቶች ለግል ወሬ እና ለመዝናኛ አገልግሎት ብቻ የዋለ መድረክ ሆኖ በብዙዎች ይቆጠራል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚደረጉ ጥናቶች እንዲሁም እንቅስቃሴዎች እንደሚያሳዩት ማህበራዊ ድረ-ገጾች ጠቀሜታቸው ሰፊ እና ለታላላቅ ተግባሮች መሳሪያ እንዲሆኑ ነው፡፡ በሰለጠነው ዓለምም የፕሬሱን ሚና እስከ መጫወት እንደደረሱ በግልፅ የምናየው ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹን በተመለከተም እንድ በፈረንጆቹ በታህሳስ 2014ዓ.ም. የተደረገ ጥናት እንደሚገልፀው በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ነው፡፡ በአገራችንም ያለው ገፅታ በቁጥር ለማስቀመጥ ጥናት ቢያስፈልግም የበይነ መረብ ተደራሽንት ከምንግዜውም በተሻለ ፍጥነትና ጥራት እያደገ መምጣቱን ጨምሮ በዙሪያችን የምንመለከተው የቀን ተቀን ገጠመኞቻችን የሚነግረን ግን ማህበራዊ ድረ-ገጾችን መጉብኘት በብዙች ዘንድ እየተለመደ የመጣና የህይወታችን አንዱ ገፅታ እንደሆነ ነው፡፡ እንግዲህ ከበዛው የማህበራዊ ድረ-ገጾች ጥቅምና አገልግሎት ውስጥ እዚህ ላይ ትኩረት የተደረገበት ጉዳይ ትምህርታዊ ፋይዳ ሲሆን በዚህ ረገድም ማህበራዊ ድረ-ገጾች በሰለጠነው ዓለም ለትምህርት ትልቅ መንገድና መድረክ በመሆን በተለይም ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቶች ብዙ ጥቅምን ሲሰጡ ታያሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት