Test Drive April 2015 | Page 5

ፈዋሽ የልብ ነገር… እስቲ ልብ ህመም በቅድሚያ የሚያሳያቸውን ምልክቶች እንመልከት ልቤን ቆረጠኝ፣አመመኝ በርካታ ጊዜ ብለን ይሆናል፡፡ልብና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ብቻ እንደሚበጣ የሚገምቱ አሉ፡፡የህክምን ባለሙያዎች ይህ ስህተት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡የሰው ልጅ ከተወለደበት ቀን አንስቶ እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ ሊያጠቃው የሚችል በሽታ ነው፡፡ ሁለት አትሉም…. ይሁን እንጂ በተቻለ መጠን ለህመሙ እንዳንጋለጥ ጥንቃቄ ማድረግ አንድ በሉ…. ∑ ∑ ∑ ∑ ∑ ∑ ∑ ∑ ∑ በመደበኛነት ደምን መለካት(ከ120/80 ከፍ ካለ ሁኔታው አሳሳቢ ነው፡፡) በሰውነት ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር(ከ40 እስከ 100 የኮሌስትሮል መጠን መደበኛ(normal)ሲሆን ከዚህ ከበለተም ካነሰም አደጋው ያመዝናል፡፡) የስኳር ህመም ምርመራ ማድረግ በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ እንቅስቃሴ ማድረግ ከ24 ሰዐት ውስጥ 7ቱን በእንቅልፍ ማሳለፍ በቀን 6 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ(የቅባት፣የኮሌስትሮል፣የካሎሪና ካርቦሀይድሬት መጠናቸው ዝቅተኛ የሆነ ምግቦችን መመገብ) ፈጣን ምግቦችን(fast food) አዘውትሮ አለመመገብ ሲጋራ አለማጨስ እነዚህ መከላከያዎች ለሁሉም እድሜና ጾታ የሚሆኑ ናቸው፡፡በተለይ ግን እድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በጾታ ብናየው ደግሞ ሴቶች ወገባችሁ ከ35-40 ኢንች…..ወንዶች ደግሞ ከ40-45 ኢንች እንዳይበልጥ ተብላችኃል፡፡ ሴቶች ላይ የሚታዩ ምልክቶች ∑ ∑ ∑ ∑ ∑ ደረት አካባቢ ህመም መሰማት ወይም በተያያዘ በክንድ፣በአንገትና መንጋጋ አካባቢዎች የሚሰማ ህመም ማስመለስን ያልተለመደ የአካል መዳከም እንቅስቃሴ ሲደረግ ወይም ተንጋለው ሲተኙ የሚፈጠር የትንፋሽ ማጠር(መቆራረጥ) የድብርት ስሜት መሰማት የእንቅልፍ ማጣትና ምቾት አለመሰማት ወንዶች ላይ የሚታዩ ∑ ∑ ∑ ∑ በደረት አካባቢ ምቾት ማጣት የትንፋሽ ማጠር የደም ግፊት መቀነስ በዚህ ምክንያት የሚፈጠር የራስ ምታት ህመም ቀዝቃዛ ላብ ማላብና የድብርት ስሜት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡