Test Drive April 2015 | Page 20

ይታጣባቸዋል መምህራኑም ቤት ሄደን አንጠራቸውም ሲሉ በምሬት ይናገራሉ፡፡ ይሄ በከተማ ነው፡፡ አድጓል፡፡ የተማሪዎች ቁጥርም እንዲሁ በቀላሉ ከ 30 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን ብቻ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከከተማ ወጣ ሲባል ደግሞ ችግሩ ከዛም ይከፋል፡፡ በከባድ ማስጠንቀቂያ እና ማስፈራሪያ ከመሰረተ ትምህርት መስጫው ክፍል የተገኙ ተማሪዎች ያንጎላጃሉ፡፡ #ሀ; በሉ ይላል መምህር ፊደል ላይ ጠቁሞ እንዴ #ሀ;ንማ ድሮም እናውቃታለን ከብቶቻችን ስናግድ ሀ እያልን ነው፡፡ ምን አዲስ ነገር አለው ይነጫነጫሉ፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም ዕውቀትን ለማግኘት ብዙ ርቀት መጓዝ የሚያስፈልግባቸው ሂደቶች አሉ፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ በሩ አከባቢ የተቀመጡ አንድ አባወራ ሹልክ ብለው ይወጣሉ 30 ደቂቃ ሳይሞላ ክፍሉ ባዶ ይቀራል፡፡ ተሰብሳቢው በጠላ፣ አረቄ ቤት ይገኛሉ፡፡ መምህር ተጠያቂ ነውና መርቶ ያሲዛቸዋል የእገሌ ልጅ አሳሰረን….. ሲሉ መምህሩ ላይ የእርግማን ናዳ ያወርዳሉ፡፡ ሴቶች በርካታ ሴት ህፃናት ዛሬም በጾታ እኩልነት በማያምኑ ሰዎች አፈና፣ ጭቆናና በደል ይደርስባቸዋል፡፡ የሴቶችን እኩልነት መቀበል ካቃተው አባወራ አንስቶ እሰከ ማህበረሰብ ድረስ ዛሬም ወደ ትምህርት ቤት ለሚያመሩ ሴቶች እንቅፋት ሆነዋል፡፡ ወንድ ልጅ ወደ ጨዋታ ሴት ልጅ ወደ ውሃ መቅዳት ፤ ወንድ ልጅ ወደ ትምህርት ቤት ሴቲቱን ወደ ማጀት የሚልኩ ወላጆች ዛሬም አሉ፡፡ ህፃናትና ሴቶችን ከገጠር የአገሪቱ ክፍል በማምጣት ከትምህርት ገበታ በማግለል ከእድሜአቸው 3 እና 4 እጥፍ የከበደ ስራ የሚያሸክሙ ግለሰቦችና ደላሎች የጉዞው እንቅፋት ሆነዋል፡፡ በርካታ ሴት ተማሪዎች ከቤት ወደ ት/ቤት የሚያደርጉት ጉዞ በተለያዮ ጾታዊ ጥቃቶች ደናቀፋል፡፡ በሱስ የናወዘ፣ በወሲብ ፊልም የዛገ አዕምሮ በጠራራ ፀሐይም በምሽትም ነገ ብዙ ይደርሳሉ የተባሉ ሴት ህፃናትና ታዳጊዎችን ተስፋ አጨልሟል፡፡ እያጨለመም ነው ፡፡ የኑሮ ደረጃ እናም የመሰረተ ትምህርት መርሃግብር ስኬቱ የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም የተወሰኑ ማንበብና መፃፍ…. ከዛም በላይ መድረስ የቻሉ ኢትዮጵያውያንን አፍርቷል፡፡ በደርግ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትም 34% የደረሰበት ጊዜ እንደነበር በወቅቱ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ምንም እንኳን በዘመን ከፍተኛ የመምህራን ዕጥረት የነበረበት ቢሆንም ለዚህም 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች በአስተማሪነት እንዲያሰማሩ መደረጉ የታወሳል፡፡ የሴት ልጆች እኩልነት እና በትምህርት ተሳትፎ እንዲቀጥል ጥረት የተደረገበት ጊዜም ነበር ፡፡ የሴቶች ተማሪዎች ቁጥር በመጠኑም ቢሆን ከፍ ያለበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ዘመን ጥቂት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመኖራቸው ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ጠባብ ዕድል ነበር፡፡ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ ሁኔታም በዩኒቨርሲቲ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የነበሩ ተማሪዎች ተምረው አገራቸውን ማገልገል እንዳይችሉ እንዳደረጋቸውም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህ ዘመን ለትምህርቱ ዘርፍ ያበረከተው ሚና ቀላል ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ያለፉ በርካታ ዛሬም አገራቸውን እያገለገሉ የሚገኙ ግለሰቦች መኖራቸውን ልብ ማለት ያሻል ፡፡ እውቀትን ለማግኘት ምን ያህል ጥረት እንዳደረጉም ከእነርሱ መረዳት ይቻላል፡፡ አሁን ኢትዮጵያ በ 1983 ዓ.ም በኢህአዲግ ስርዓት መተዳደር ከጀመረች በኋላ በትምህርት ዘርፉ ትላልቅ ለውጦች የታየበት ጊዜ ነው፡፡ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብዛት የኑሮ አቅማችን ዛሪም ለትምህርቱ ዘርፍ መሰናክል መሆኑ አይካድም ፡፡ ምናልባት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያለው ትምህርት ላይ ያለው ተፅዕኖ ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ዝቅተኛ ነው ሲባል ተፅዕኖ የለውም ለማለት እንዳልሆነ ግን ይታሰብልን፡፡ ቁርሳቸውን ሳይበሉ ወደ ት/ቤት የሚመጡ ህፃናት በረሃብ ሲያንጎላጁ ከጉናቸው ቁጭ ብለው ተመልክተናል፡፡ መማሪያ ደብተርና እስኪርብቶ አጥተው ከትምህርት ቤት የቀሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከአዲስ አበባ ወጣ ስንልም እበት ጠፍጥፈው ከብቶችን በማገድ የትምህርት ገበታን ማየት ያልቻሉ አሉ፡፡ በአዲስ አበባም ከእድሜ እኩዮቻቸው ያነሰ ኑሮ ስላላቸው ማታ ማታ በየመጠጥና መሸታ ቤት ማስቲካና ሲጋራ እያዞሩ ቀን ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡስ ምን ያህል ናቸው? የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የምዕተ አመቱን ግብ አፈፃፀም በ2006 ሰኔ ወር ላይ ባቀረበው ሪፖርት የመጀመሪያ ደረጃ