Test Drive April 2015 | Page 19

በከተማ የሚኖሩ ወጣት እና ታዳጊዎች ትምህርት ማግኘታቸው ዕድል ሰፊ ነበር፡፡ በተመሳሳይ በኑሯቸው የተሻሉ የነበሩት ተማሪዎ ጥሩ ትምህርት ማግኘት እድሉ ነበራቸው፡፡ ስለ ዘመኑ ስንናገር በባላባት እና በጭሰኛው ልጅ መካከል የሚደረገው የትምህርት ቤት ፉክክር የሚጀመረው ሁለተኛ ደረጃ ሲገቡ ነበር ፡፡ በልዩ መልክም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በትምህርት አቀባበላቸው ላቅ ያሉ ተማሪዎች የሚሰባሰቡበት ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤትን ማስታወስ ይቻላል ፡፡ በኋላም በ 1942 ዓ.ም የተመሰረተው በዘመኑ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ሃይማኖታዊ ብሂሎች እና የኑሮ ደረጃዎች የተውጣጡ ተማሪዎች ያስተናገዱ ተቋማት ነበሩ ፡፡ እዚህ ጋር የሁለት ወንወድማማቾችን ታሪከ ላንሳ ምናልባት ታሪካቸው የብዙ ኢትዮጵያውያን የዘመኑ ወጣቶች ታሪክ ይሆናል፡፡ እዚህም ላይ የኑሮ ደረጃቸው ሳይበግራቸው በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ሁሉ ተቃቁመው ከአገር መሪነት አንስ