Test Drive April 2015 | Page 21
ይህ ቁጥር ከ2000 ወደ 2006 በ19 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል፡፡
በዚህ በርካታ መጠነኛ ክፍያ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ የህዝብ
ት/ቤቶች ወደ መንግስት ትምህርት ቤትነት ተለውጠዋል፡፡ ይህ
እጅግ መልካም የሚባል ነው ይሁን እንጂ ዛሬም ከት/ቤት የተለዩ
ህፃናት አሉ፡፡
የኑሮ ልዩነት አፍጦና አግጦ የሚወጣው ከሁለተኛ ደረጃ በኋላ
ነው፡፡ ከጥሩ ቤተሰብ የተገኙ ልጆች መሰረታዊ ፍላጉታቸው
ተሟልቶላቸዋልና ሌሎች ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ይንቀሳቀሳሉ፡፡
ተሳክቶላቸውም ወደ ግባቸው ሲያመሩ እያስተዋልን ነው ፡፡
ሱስ
በሁለተኛ ደረጃዎችና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሱሰኛ ተማሪዎች ቁጥር
ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ አንድ ቤተሰቡን የሚያስብ፣ አገሩን
የሚያስብና የነገን ብሩህነት የሚረዳ ተማሪ እንዴት ወደ ሱስ ይገባል
ሌላ ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ ሱስ ሲባል የመጠጥ፣
የሲጋራ፣ የጫት፣ የአደንዛዥ እጾች ብቻ ሳይሆን የወሲብ ሱስም
ውስጥ የተዘፈቁ ብዙ ወጣቶች አሉ፡፡
በአንድ ወቅት መምህር ነበርኩ ያስተማርኩትም ከፍተኛ ገቢ ያላቸው
ቤተሰቦች ልጆቻቸውን የሚልኩበት ቤተ ትምህርት ነበር፡፡ እናም
መምህርነቴን ካቆምኩ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ነው አንድ ቦሌ የሚገኝ
መጠጥ ቤትና ሬስቶራንት በጋራ የሚሰጥ ቤት ውስጥ አልኮል
መጠጥ ይዘን ቁጭ ብለናል፤ እኔ ካለሁበት ሦስትና አራት ጠረጼዛ
በኋላ አንዲት ሴት ልጅ ወደኔ መጣች ቲቸር አለቺኝ እጅግ ደነገጥኩ
ተማሪዬ ነበረች ጥቂት አወራኋት በኋላ ወደ ጠረጼዛዋ ተመለሰች ፡፡
ሦስት ሴቶችና አራት ወንዶች ናቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከ
18 ዓመት በታች እናም አይኔን አሻግሬ ስመለከት እኔ ከያዝኩት
መጠጥ አይነት አልኮሎችን ይጎነጫሉ ፤ ሲጋራ በላይ በላዩ ያጤሳሉ
ምን ማለት እንደምችል ለጊዜው ማወቅ አልቻልኩም፡፡ ብቻ አንድ
ሀሳብ አይምሮዬ ላይ መጣ ለምን ትጠጣላችሁ ብዬ ልጠይቅ፤ የለም
አንተስ ለምን ትጠጣለህ የሚል ምላሽ ቢመጣስ፡፡
አወይ መምህር ላይ ያለበት አባዜ
የተማሪ አስተዋይ በጠየቀው ጊዜ
የሚለውን ግጥም ልቀይረው አሰብኩ እናም እነዚህ ልጆች ከቤተሰብ
የሚያገኙት ገንዘብ እጅግ የበዛ ስለመሆኑ ከእኔ በላይ ምስክር
የለም፡፡ በተቃራኒ ደገሞ የሴትነት መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት
ያልቻሉ ሴቶች እንዳሉም ልንረሳ አይገባም፡፡
በተለይም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ሳሙና፣ የንፅህና መጠበቂያዎችና
ወረቀቶችን ማሟላት ከማይችሉ ቤተሰቦች በመገኘታቸው ብቻ
ከዕድሜ እኩዮቻቸው ላለማነስ በዕድሜ በሁለንተና በሦስት እጥፍ
ከሚበልጧቸው ባለሃብቶች አዛውንቶች ጋር ያልተገባ ግንኙነት
የሚያደርጉ ወጣት ሴቶችም እንዳሉ ምስክር መጥራት
አይኖርብኝም፡፡
ማጠቃለያ
ግን ግን በቅድሚያ ማህበረሰቡ፣ ቀጥሎ መንግስት ጠበብ ስናደርገው
ደግሞ ቤተሰብ ለልጆቹ አስተዳደግ ያለው ሚና ከፍ ያለ ነው፡፡
እናም ሁሉም በአንድነት እና በተናጠል ከዚህ በላይ ብዙ መስራት
አለባቸው፡፡ ማህበረሰቡ ልጄ የሚለው በቤቱ ያለውን አልያም
ከአብራኩ የተከፈለውን ብቻ መሆን አለበት በዬ አላምንም ፡፡ በቤቱ
18 ዓመት የሆነ ታዳጊ መጠጥ ሲያዝ ያዘዘው መጠጥ ከሚያሰገኝለት
100 እና 200 ብር የበለጠ የትውልድና የአገር ሁኔታ የሚያሳስበው
ማህበረሰብ ማየት እፈልጋለሁ፡፡
መንግስትም ዛሬ ከሰራቸው በርካታ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ
ሌሎችን ማህበራዊ ጉዳይ ላይ መስራት ይኖርበታል፡፡ የትምህርት
ጥራቱና የተማሪዎች ስነ-ምግባር ላይ ብዙ መሰራት አለበት ቤተሰብ
የሁሉም ነገር መሰረት ነውና ብዙ ይሰራል ብዬ አስባለሁ፡፡
እነዚህን መሰናክሎችና እንቅፋቶች ሁሉ አልፈው ግን ዛሬም
ከእውቀት፣ ከትምህርትና ከምርምር አምባ የሚገኙ ለአገራቸው
ተስፋ የሚሆኑ በርካቶች ናቸው፡፡
እውነት ትምህርትን ለማግኘት ምን ያህል ይፈጃል………ብዙ…….ብዙ