Test Drive April 2015 | Page 16

ለሰው ክብር ማጣታቸው ብቻ ጎልቶ፤ ጨዋና አገልጋዮቹ ተረስተው ሁሉን በአንድ ቁና ሰፍሮ በአንድ ሚዛን መመዘን ይቀናናል፡፡ ከተሳፋሪስ ስንት አይነት ምግባረ ብልሹ አለ? ሳይከፍል “ከፍያለሁ” ብሎ ድርቅ የሚል ከተሳካለትም አረሳስቶ የሚወርድ አደባባይ ላይ “ወራጅ አለ” የሚል ለምኖ ተለማምጦ ትርፍ ከተጫነ በኋላ ትራፊክ ሲመጣ የክሱን ወረቀት ለመፃፊያ ብእር የሚያቀብል፡፡ እኔ በበኩሌ ለ5 እና 10 ሳንቲም ብሎ መጨቃጨቅ እና መመናጨቅ መብት ከሆነ ይቅርብኝ በገንዘብ የማየገኘውን ንፁህ ስሜት ማደፍረስ በቁጣ መሞላት መሰደብና መሰዳደብ መብ