Test Drive April 2015 | Page 15

ፈታ በሉ ‹‹ሰሌዳው ተበይዷል›› ታክሲ ውስጥ ነኝ፡፡ ከሹፌሩ ኋላ፡፡ማለዳ 1ሰአት አካባቢ፡፡ሁሉ ወደየጉዳዩ ለመሄድ ከቤቱ የሚወጣበት ሰአት በመሆኑ ከመነሻው በመግባቴ ጥሩ ቦታ አገኘሁ እንጂ በየጎማውና በየሞተሩ ላይ ተቀምጦመሄድ ልማዴ ነበር፡ መቼ እንደጀመረኝ እንጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለድምፆች ትኩረት እሰጣለሁ፡፡በሙዚቃ መሃል በሰዎች ንግግር መሃል ለብዙዎች ያልተሰሙ ቢሰሙም ችላ ተብለው የሚታለፉ ድምፆች ጎልተው ይሰሙኛል፡፡እዚህም የመኪናው ሞተር ይጮሃል፡፡አልፎ አልፎ ከታክሲዋ ሆድ በሚወጣው ጡሩምባ ታጅቦ ችፍፍፍ የሚል የሃምሌ ዝናም ከጣሪያው ይሰማል፡፡(በበጋው ወቅት ወደ ሰማይ የተነነውን አቧራ ያየ ተጠራቅሞ ዘንድሮ በክረምት ከአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ጭቃ እነደሚዘንብ ቢተነብይም ትንቢቱ አልሰራ ኖሮ ይኸው ቀደሞ የምናውቀው ዝናም ራሱ ከሰማይ ይወርዳል)፡፡ ጋቢና ከሹፌሩ አጠገብ የተቀመጠው ሰው ትከሻውን እያርገፈገፈ ያለማቋረጥ ይስላል-ብርዱ ነው መሰል፡፡እዛው ጋቢና ከሱ በስተቀኝ ያለው ብላቴና ኪሱን እየዳበሰ ”ከዚህ ሜክሲኮ ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀ አንገቱን ወደ ሹፌሩ አስግጎ፡፡ ግን ያ ባለላፕቶፑ ሰውዬ ዩኒቨርሲቲ ግብቶ አካውንቲንጉን ሲማር ይህ የታክሲ ረዳት የት ነበር? ምናልባት የትምህርት ቤት ደጅ ከረገጠ አመታት ተቆጠሩበት ወይም በጭራሽ ትምህርትቤት ሄዶም አያውቅ ይሆናል ፤ ምናልባትም ያልጅ ነገን በተሻለ ለመጠበቅ ገንዘብ ሲቆጥብ ቁርሱን አልበላ ይሆናል፤ምናልባት ደግሞ ታማሚ እናት እና የሱን እጅ ጠብቀው የሚያድሩ ታናናሾች ይኖሩት ይሆናል፤ምናልባትም ያቺ ዘንካታ ክብደቷን ለመቀነስ ያልበላቸውን እራት ትርፍራፊ እንኳን አጥቶት ፆሙን ያደረ ይሆናል፤ ምናልባትም ያ ልጅ…ታዲያ እኛ ማን ነን? ያልዘራነውን፤ ያላረምነውን ልናጭድ ማጭዳችንን ስለን የምንወጣ? እን