Test Drive April 2015 | Page 14

ስነ-ልቦና የአኗኗራችን ነገር እኒህ ሰው የ 59 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡ ከታዋቂው የሲ ኤን ኤን የቢዝነስ ዘጋቢ ሪቻርድ ኩዊስት ጋር ፊት ለፊት ቁጭ በለው ይነጋገራሉ፡፡ ሰውዬው ብላክ ቤሪ ዘመናዊ ስልኮች አምራች ኩባንያ ቺፍ ኤክስክውተቭ (ዋና ኃላፊ) ናቸው፡፡ ጆንቼን ይባላሉ ዋልት ደዝኒ የመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎችን ያስተዳድሩም ናቸው፡፡ ጄን በዓመት ውስጥ እጅግ ጥቂት ቀናት ብቻ በእረፍት ያሳልፋሉ፡፡ እሳቸው ከ3 አና ከ4 ቀን አይበልጥም ባይ ናቸው፡፡ ሰውዬው በዓመት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ እናም ጊዜያቸውን በሙሉ በድርጅቱ ስራ ላይ ያሳልፋሉ፡፡ ሪቻርድ ኪዊስት ጠየቀ ፡- ከስራ ውጪ ጊዜ ምትሰጠው ጉዳይ ምንድነው? ጆን ቼን መለሱ ፡- ከስራ ውጪ ለሁለት ነገሮች ጊዜ እሰጣለሁ ከ 24 ሰዓቱ 2 ወይም 3 የሚሆኑትን ሰዓታት የመጀመሪያው ለቤተሰቦቼ የምሰጠው ጊዜ ሲሆን ሌላው ለንባብ የምሰጠው ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ ጊዜያት ከስራም ከቴክኖሎጂ ውጤቶችም ነፃ የሆኑ ናቸው፡፡ ቴሌቭዥን፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ አይ ፓድ ከመሳሰሉ በህይወቴ በየእለቱ ከሚያጋጥሙኝ ነገሮች የምርቅበት ነፃ ጊዜ ናቸው አሉ ሚስተር ቼን ፈገግ ብለው፡፡ እኔም ከቴክኖሎጂ ጥገኝነት (Technological dependency) ነፃ የምሆንበት ጊዜ በመሆን እጅጉን የምወደው ሰዓት ነው አሉ ቼን፡፡ የጆን ቼንን ሃሳብ ያነሳሁት እሩቅ ሳትሄዱ እዚህ ያለን የኢትዮጵያውያን ህይወትም በቴክኖሎጂ የተከበበ ሆኗል፤ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ ስጦታዎቻችንን ለመጠቀም ፈፅሞ እየሰነፍን ነው፡፡ ማለዳ ከእንቅልፋችን ተነስተን ማታ ወደ መኝታችን እስክንመለስ ድረስ ምን ያህል ህይወታችን ከአዳዲስ እና ነባር የፈጠራ (የቴክኖሎጂ) ውጤቶች ጋር እንደተሳሰርን ለአፍታ አስበነው እናውቃለን፡፡ ባለሱቁ በእጁ የሂሳብ ማሽን (ካልኩሌተር ካያልዙ) ሂሳብ ድሮ ቀረች…… የሂሳብ ደብተርም እንዲሁ፤ የስልክ ቁጥር መመዝገቢያ ደብተር ያላቸው ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ማስታወሻ አይፓዶቻቸው ላይ እንዳፈጠጡ ቀኑ ይመሻል፡፡ እናም ወዳጄ እንዲህ አለኝ ቤተሰቡን ስትገልጸው ይህ በቤተሰብ መካከል ሀሳብ መለዋወጥ መነጋገር መደማመጥ የሚባሉ ነገሮች ጠፍተዋል ፡፡ አብረው እየኖሩ አብረው አይኖሩም፡፡ እኔም በእሳት ዳር ሰብሰብ ብለው መረጃን የሚለዋወጡ፣ የአገሩን ታሪክና ቅርስ የሚያወራ ወገኔ በአይምሮዬ ብቅ አለ፡፡ ወይ ነዶ….ወይ ንዶ….. ደብተርም ዛሬ የለም ተንቀሳቃሽ ስልካችን ብዙ ነገርን ፈታ ፤ ብዙ ነገሮችን አቃለለ፡፡ ግን፤ ግን ለ 10+5 ሁሉ ቴክኖሎጂ የምንጠቀም ነገር አልመሰላችሁም፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ጥገኝነት (dependency) ሚባለው ሊሆን እንደሚችል እና በምክንያቶች የተሞላ ነው፡፡ በውስጡ ብዙ የጥገኝነት አይነቶች ይይዛል፡፡ የግብ ጥገኝነት (Goal dependency) ፣ የተግባር ጥገኝነት (Task dependency) እና የግዴታ ጥገኝነት (Hard dependency) ን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ይጥገኝነት ሁኔታዎች መልካም ነገሮችን በመፈለግ ስለሙያው (ሰለስራው) ለማወቅ በመፈለግ የሚደረግ እና አንዳዴ ደግሞ ሰዎች አማራጭ በማጣት የሚፈፅሟቸው ጥገኝነቶች ና