ቅፅ_2_ቁጥር_10 | Page 32

ጸሐፊ ሁሴን ይመር

ጸሐፊ ሁሴን ይመር

የቤሰብ ወግ

በእድሜ ትንሿ ጀግኒት

ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው አለ የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ “ ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ? “ ‹‹ አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው ፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ ኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ ፡ ፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት ፡፡ በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ ፡፡ ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት ፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ ፡፡ ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት ፡ ፡ ከዚያም አወከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል ፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት ፡፡ ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ እኔም “ ለምን ? “ አልኩት :: እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው ፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው ፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ ፡ ፡” አለው ። ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው ፡፡” እንዲል አደረገው ።
ታዲያ ይህ የቢልጌትን የሀብት መጠን ወይም ባለጠጋነቱን እንዳያሥብ ያደረገው ሳይኖረው ከሌለው ላይ የሠጠው ጥቁር የገንዘብ እንጂ የመሥጠት ሃብታም እንዲየውም ቁጥር አንድ ቱጃር እሡ ነው ብሎ መሥክሮለታል ። ለመሥጠት ሃብታም መሆን አያሥፈልግም ፣ ከልብ ለጋሥ ለሆነ ሠው ።
“ ለሁሉም ግዜውን ይጠብቅለታል
በማለት ሠለሞን ቀድሞ ተናግሮታል ! “ ብሎ ነበር ያዜመው ክቡር ዶ / ር አርቲስት መሐሙድ አህመድ ። የኛነታችን ምሥጢር ከግዜ ጋር መሥተጋብር ፈጥሮ ትናንት ከትናንት ወዲያ አምና ፣ ካቻምና ፣ ዘንድሮ ቀን እና ለሊት በሚል የመሥፈሪያ አሊያም መዘወሪያ ግዜያችንን የምንጠብቅ ሥንቶቻችን እንሆን ? መልሱን ቤት ይቁጠረው ። እኛ የሠው ልጆች ወደዚህችኛይቱ ዓለም ስንመጣ ኖሩ ሞቱ ከሚባሉ ሠዎች ጎራ ላለመመደብ ምን ያህል እኛ ሥለራሳችን ሥለቤተሰቦቻችን ሥለጎረቤት ሥለ ሠፈራችን ሥለማህበረሠቡ እንዲሁም ምን ዓይነት በጎ ፋይዳ ያለው ሥራ ሠርተን እንድናልፍ አሥበን አሊያም ተመኝተን እናውቃለን ህይወት በራሷ መንገድ የምታሥተምርበት በርካታ እውነታዎችን ማሳያ የሚሆኑ ጥቂት ሠዎች አሉ ።
ለዛሬ ከላይ እንደመንደሬደሪያ ብዬ ያቀረብኩትን ፅሁፍ የሚያጠናክርልኝ ነውና አብራችሁኝ ሁኑ ። በዚህ ፅሁፌ እኔ አዲሥ አበባ ላይ ቁጭ ብዬ መጀመሪያ ወደጎንደር ከዛ ባህርዳር ይዣችሁ ልጓዝ ነው ። ሊቦ ከምከም አዲስ ዘመን ትውልድ ስፍራዋ ነው ። ሠአዳ ንጋቴ :: ልጅ ሁና አርቆ አስተዋይ እና የልጅ ባህሪ ሳይሆን የአዋቂ አይነት ባህሪ ነበር የምታሳየው ። ማህበራዊ ኑሮ የልጅነት ልምምድ ውጤት ይመስላል ። በቤተሰብ ውሥጥ የሚወራባት እከሌ ሞተ ከተባለ ቀብር ላይ የምትታየው ከአዋቂ እኩል በመሆኑ ነው ። ገና በአፍላ እድሜዋ የመሰረተቸው ትዳር አልሰመረም ነበር እና የስደትንም ህይወት ለማየት ህይወት አስገድዷት ነበር ። በወቅቱ በኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ላይ የሚደርሥባቸው እንግልት እና ሥቃይ እንቅልፍ ቢነሳት ወደሃገሯ ተመለሰች ።
ቅንድል መፅሔት ቅንነት ድል ያደርጋል ! ገጽ 32