ሕብረ፥ቅላጼ / SIDE Attractors of Meanings & SOCIAL HARMONY | Page 21
ሕብረ፥ቅላጼ
የሕይወት ትርጉሙ / ፍሬ፥ነገሩ
ሕይወት ማለት፣
የእግዚአብሄርን፣ ማለትም የፈጣሪነትን ብቃት፣ በሁሉም የተፈጥሮ ጉዳይ ውስጥ እየቀሰቀስ፣ሰብዓዊ፣ ሁለንተናዊ ና
የሰው፥ዘር ኪነ፥ውበታዊ ተፈጥሮን የሚያድስ፣ አያሌ ዘርፍ ያለው የተወሳሰበ የተፈጥሮ ሂደት ነው። የዚህም ማሳረጊያ
ግቡ፣ብዙ ትውልድን እያሸጋገረ በህብራዊነት የሚካነውን የሰው ልጅ መፍጠር ነው።/1
የሕይወት ፍሬ ነገር የሚገኘው፣
1ኛ፣ በማህበራዊ መስክ
2ኛ፣ በባህላዊ መስክ
3ኛ፣ በቁስ፥አካላዊ መስክ
4ኛ፣ በመንፈሳዊ መስክ
ውስጥ ሲሆን፤ እነዚህን የሚያዋስኑ መለኮታዊ ድንበሮች ደግም አሉ፥
ክእነዚህ መስኮች አብራክ ወጥቶ የሚከሰተው፣
5ኛ፣ የሰው፣ ልጅ መስክ እና
ከሁሉም መስኮች ጋር ተዛምዶ የሚስተጋበረው፣
6ኛ፣ ሁለንተናዊ መስክ።
(መስኮች፣ በሚያያዙ ማስተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ (Planes: “the conjunctive syntheses”/2))
ለእነዚህ መስኮች፣ እንደ ጀርባ ምሶሶ ሆነው የሚቆሙና የሚያገለግሉ ስምንት አድማሶች ወይንም መለኪያውች አሉ።
( አድማሶች፣ በሚያያይዙ ማስተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ፣(Dimensions: “the connective syntheses”/2))
1ኛ፣ ስነ፥መንግሥትና ሕግ
2ኛ፣ ማህበረሰብ ና ስነ፣ምግባር
3 ኛ፣ ቤተሰብና ፍቅር
4ኛ፣ የሰው፥ልጅ ና ተስፋ፥ብርሃኑ
5ኛ፣ የሰው፥ዘርና ሕሊና
6ኛ፣ ስነ፥ፍጥረትና ሃይማኖት
7ኛ፣ ሰማያታትና ዕምነት
8ኛ፣ እግዚአብሄር/ ሁለንተናዊነት ና ምሕረት
በነዚህ አድማሳት መሃከል አያሌ የሚያወራረሱና የሚያጠላለፉ አገናኝ ከፍሎች ሲኖሩ፣ እየተቀባበሉ እርስበርስ
የሚያነቃቁ መስተጋብሮችም አሉ።
(ተወራራሽ ፥ ክፍሎች፣ በሚስተያዩ/ በሚመዛዘኑ ማስተሳሰሪያዎች ይቀላጠፋሉ፣(Cross‐sections: reflective syntheses))