ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 8
“ምሁሩ አንስተው መጽሓፉ ውስጥ ያገኙትን ምርጥ ቨርቺውስን
ቆጥረውልናል።
እዚያው ላይ „ እንደ ደፋርነትና እንደ ተስፋ እንደ ጥንካሬና እንደ ሥራ
ወዳድነት እንደ ትህትና እና እንደ ደስታን እንደ ፍርድና ፍትህ…እንደ
ጥራትና እነደ ቻይነት- እንደ ልበ-ሰፊነት እንደ መቆጠብና
ከስግብግብነት መራቅን እነደ አክብሮት እነደ አርቆ ማየት ….እነደ
እምነትና ጠንካራ ሃይማኖታዊነት….“ያሉትን ፕሮፌሰሩ ሰብሰብው
ያስቀመጡትን ውድ ሐብቶች እዚያም ውስጥ እናገኛለን።
„ተግሣጽና ምክር „የሚባሉ ጽሑፎች ነበሩ። የሞራልና የግብረገብ
ትምህርት በየትምህርት ቤቱ ለወጣቱ ትውልድ ይሰጥ ነበር።
„መልካም ሶሳይት“ የሚባሉ የሥነ -ስርዓት ማስተማሪያ ጽሑፎች ነበሩ።
እዚያም ላይ „የአቀራረብና የአነጋገር የአቋቋምና የአቀባበል ቅደም
ተከተል የትህትና እና የአክብሮት ሥነ-ስርዓቶች“ ለልጆች ይተላለፉ
ነበር።
ይህ ሁሉ ግን ወይ „አብዮት“ በሚባለው ነገር ወይም“ አብዮታዊ
እርምጃ …“ በሚባለው አዲስ „ባህልና ጌጥ“ ድረሻቸው እንዲጠፋም
ተደርጎአል።
የአገር ፍቅርም በዚያው አብሮ በተወሰኑ ሰዎች ዘንድ መሬት ላይ ተጥሎ
ተረግጦአል።
እሴት እና አይዲኦሎጂን በመጽሔቱ ላይ ያነሳነውም ከዚህ አንጻር ብቻ
ነው።
ሰዎች በዘር ወይም በአጥንት ቆጠራ ላይ ተመስርተው በኢትዮጵያ
ከሚደራጁ -ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው- (እንደ ጤፍ
የተደበላለቅን ስለሆን አንዱን ፍሬ ለቅሞ ከሌላው መለያያቱ ከባድ
ነው)- በተለያዩ አይዲኦሎጂ ዙሪያና ሥር እንደ ሌላው የዓለም ሕዝብ
ተሰባስበው ቢደራጁ እኛ የምንቃወመው ሳይሆን የምንደግፈው አካሄድ
ነው።
8