ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 7

የኢትዮጵያ ባህልና ትውፊት (ካልቸርና ትራዲሽን) የተመሰረቱት በዚህ እላይ በአነሳነው በትሩፋትና አገሪቱ ከጥንት ጀምሮ በምትመራበት ሥነምግባርና ግብረገብም (ሞራልና ኤትክስም) ነው። እነዚህ ሁሉ አብረው የተያያዙ ናቸው። በሁዋላ ግን ሳይታሰብ ብቅ ያሉ አሁንም እየተጠናከሩ የመጡ አዲስ አመለካከቶች የነበረውን ሁሉ እንዳልነበር አድርገዋል። „ማጭበርበር፣ መዋሸት፣ መስገብገብ አለመደማመጥ …እግዚአብሔርን አለመፍራት …በአጭሩ አብዮታዊ እርምጃየሚባሉ ነገሮችና….ፍርደ ገምድልነትየሚሊተሪ የጦር ሜዳ ፍርድ “ የሚባሉት ጠበንጃ ለያዙት ብቻ የሚሰራና የሚያገለግል አዲስ ኖርሞችና „ሕግጋት“ …እነዚህ ሁሉ የተጻፉና ያልተጻፉ የአኗኗር ዘዴዎችን ገልብጠውና ገለባብጠው ነገሮችን ሁሉ -ነጮቹ እንደሚሉት-በእግራቸው ሳይሆን በጭንቅላታቸው አገራችንንአቁመው ለቀዋታል። ይመስላል እንጂ ነገሮች ሁሉ ቀስ እያሉ ከቅጥጥር ውጭ ሁነዋል። ከሆኑም ቆይቶአል። ጨርሶ መደማመጥ መግባባት በማንኛችንም ቤት የሌለው በሌላ ሳይ