ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 4
መጽሔቱ በአጠቃላይ በርካታ ነጥቦችን አቅፎአል።
ሁሉም ጉዳዮች የሚሸከረከሩትደግሞ እግዚአብሔር በሰጠን መብት –
አንዳዶቹ ይህን ነገር ተፈጥሮ ነው ይሉታል – „በኢንላይትመንትና
በሊበርቲ“ ዙሪያ ነው:- እኔም አንተም ሁላችንም ነጻ-ሰው ነን።
አንደኛው -ከወዲሁ ግልጽ ለማድረግ-ሁለት
ፍልስፍናዎችና
ትምህርቶች ከጀርመን ተነስተው „የዓለም ሕዝብ ሁሉ በዚህ ሥርዓት
ውስጥ የግድ መኖር አለበት“ ብለው አገሩቱንም ሕዝቡንም ምድርንም
በየአለበት አተረማምሰው በሃያኛው ክፍለ ዘመን እንደሄዱ የሚታወቅ
ነው።
በብዙዎቹ ዘንድ የማይታወቀው ጀርመን እነዚህን ትምህርቶችና
ፍልስፍናዎችን (ማርክሲዝምንና ፋሺዝምን) በምን ብልሃትና ዘዴ
አራግፋ ከእነሱም ተገላግላ ወደ ነጻ-ሕብረተሰብ ተሸጋግራ
በኢኮኖሚያዋ በልጽጋ ሁሉን ቀድማ ሕዝቦቹዋን አስደስታ እዚህ አሁን
የምናየው ደረጃ ላይ ደረሰች ለሚለው ጥያቄ የሰጠቺው መልስ ነው።
ይህንንም እኛ በዚህች ሕትመታችን ላይ ከሞላ ጎደል ብልሃቱንና ጥበቡን
አንስተን እናንተ እንድትመለከቱት አድርገናል።
ወረድ ብለን በዚህ በኩል አሸነፍናት ብለው ገና እፎይ ሳይሉ በሌላ
በኩል ብቅ ስለምትልባቸው ኢትዮጵያ እናነሳለን። አሁን ደግሞ
ኢትዮጵያ በኩዋክብት ተመስላ ስሙዋን ቀየር አድርጋ „ካሲዮጵያ „
ተብላ እንዴት ብቅ እንዳለች እንመለከታለን።
ስለዚህች የኢትዮጵያ ንግሥት ማንም የማይደርስባት ሰማይ ላይ
ዘለዓለማዊ ሁና ስለቀረቺው ኮከብ-„ካሲዮጵያ“ እግረ መንገዳችንን
አንስተን እናልፋለን።
ከዚሁ ጋር እንደ „ማስቲካ“ ጥዋት ማታ ስለሚታኘከው ስለ አማራና ስለ
ብሔር ብሔረሰብ እሰከ መገንጠል ድረስ ጥያቄም መለስ ብለን አንስተን
4