ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 34

ከሮማው ቄሳሮች-ኃይለኛው የዩሊዮስ ሴዛር እንኳን ያልደፈረውን ከ2 ሺህ አመት በሁዋላ አርፍዳ የተቋቋመቺው የጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን ቅኝ አድርጋ ልትገዛ ሁለት ጊዜ መጥታ ሁለት ጊዜ ድል ተመታ ወደ መንደሩዋ ተመልሳለች። እነዚህ ሁሉ ያልቻሉትን አሁን አንዳንድ ልጆቹዋ በተለያዩ ስሞች „ኢትዮጵያ“ የሚባል ነገር የለም ብለው አድመው ተነስተውባታል። ጥያቄው እነሱ ስንት ናቸው የሚለው ነው? አንድ መቶ? አምስት መቶ? አንድ ሺህ? ወይስ እነደሚፎክሩት ሁለትና አምስት ሺህ? እነሱስ በየጊዜው ምን ይላሉ? የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ነው። ምንድነው ሁል ጊዜ እንደ አዲስ ነገር የሚነሳው?የትኛውን አይዲኦሎጂ ነው የሚከተሉት? አንደኛው „የብሔር /ብሔረሰብ እኩልነት?“ የሚለው ተገቢ የሆነ ጥያቄ ነው። ሁለተኛው „…. እሰከ መገንጠል „ የሚለው ቅጥ ያጣጣጣ ነገር ነው። 34