ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6 | Page 26
አብራርተው ሕገ -መንግሥታቸው ላይ እሴቶቻቸውን ሲያሰፍሩትም
እነሱእንደዚህ ብለው አስቀምጠውታል። ከሁሉም አረፍተ ነገር ቀድሞ
በመጀመሪያ!
„…የማንም ሰው
በማንም
ሰው
አይረገጥም
„
ሰፍሮአል።
መብቱና ክብሩ
አይደፈርም
የሚለው ቃል
ቀጠል
አድርጎ
ይኸው ሕገመንግሥታቸው
„…ማንም ሰው
የፈለገውን
ሓሳቡን
በጽሑፍ ይሁን
በቃል
በወረቀት ይሁን በፊልም መልክ አቅርቦ መበተን ማሰራጨት ይችላል።
…ሣንሱር የሚባል ነገር የለም። „ ብሎ አዲሱን ዘመን ያበስራል።
ይኸው ሕገ መንግሥታቸው „መደራጀት መደገፍና መቃወም መሰብሰብ
መምረጥና መመረጥ… መመራመር…ማንም ሰው ይችላል“ ይላል።
እነዚህ እሴቶች እነዚህ ቫሊዩዎች ናቸው የአገርንና የሕዝብ አንድነትን
የሕግ በላይነትን ከሁሉም በላይ የግለሰብ ነጻነትን አረጋግጦ ጀርመንን
ዛሬ የደረሰችበት የሥልጣኔን ዕድገትና ደረጃ ላይ ያደረሳት።
ይህ ብቻ አይደለም።
የጀርመን ሕገ-መንግሥት የተመሰረተበት እሴት ሰብሰብ አድርገን
ስናየነው „…በግለ ሰብ ሙሉ ነጻነት ላይ „የቆመ ነው። እዚያም ውስጥ „
በሕግ ፊት ሁሉም እኩል “ እንደሆነ ያነሳል። „የሕዝብ ውሳኔና
ዲሞክራሲም“ በአገሪቱ እንዳለ ያረጋግጣል።
የሕገ- መንግሥቱ እሴት ነጻው ሕብረተሰብ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ
ያብራራል።
እዚያም ውስጥ የግል ሕይወትና የግል ኑሮና የመኖሪያ ቤቶች በማንም
እንደማይደፈሩ በግልጽ ቋንቋ ያነሳል።
26