ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 43

የአድዋ ድል 118ኛ ዓመት ዛሬ በየካቲት 23፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም. ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ የአድዋ ጦርነት ሲጀመር 118 ዓመት ይሆነዋል።*1 የአድዋን ድል 118ኛ ዓመት ለማስታወስ ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ና የአድዋ ገድል :_ ጀግንነትና የአዋቂ ሰው ሥራ ታሪክ የዘመናዊ ፖለቲካ አሠራር አጀማማር በኢትዮጵያ * ዜናው ተናፍሶ ወሬው ዓለምን አዳርሶ ጥቁሩንም ነጩንም ቀዩንም ፍጡር ከዚያም ራቅ ብለው የሚኖሩትንም ቢጫውንም ሕዝብ ያኔ ከነበሩት ከእነጌቶቻቸው ያስደነገጠው አንድ ነገር ቢኖር አደዋ ነው። *2 ትንሽ ቆይቶም ዜናው በቅኝ ግዛት መዳፍ ሥር ነጻነታቸውን ተገፈው የሚኖሩትን ያኔ „ባሪያዎች“ ተብለው የተናቁትን ሕዝቦች የልብ ልብ ሰጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስደሰተው በሁዋላም እንደምናነበው የታሪክ ጸሓፊዎችንም በብዙ ቦታ በጣም ያስገረመው የአደዋ ጦርነት፣ የተጀመረው በየካቲት 23 43