ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 36

በሁለተኛ ደረጃ አንድን ሕብረተሰብ የሚያስተሳስረው ነገር የጋራ ቋንቋቸውና ፊደላቸው ነው። በጋራ ያሳለፉት ታሪካቸውም ሌላው በሦስተኛው ረድፍ መነሳት ያለበት ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ያለፈውን „በደንብ የማናውቀውን „ የአያት ቅድመ አያቶችን ዘመንንም ያካትታል። ሃይማኖት ነው እንዳይባል ኢትዮጵያ በሦስት ትላልቅ ሃይማኖቶች ስለተከፋፈለች „እኛ እንደ አረቡና እ ንደ ቻይናው እንደ ሕንዱና እንደ ቱርኩ አንድ ወጥ ሃይማኖት ሁሉንም ያሚያያይዝ እምነት የለንም „ ስለዚህ „አንድ የሚያደርገን መንፈስ በመካከላችን የለም“ የሚሉ ሰዎች አይጠፉም። ይህ አባባል በትክክሉ ለመፍረድ ዕውነት ነው? ለመሆኑ ሕንዶችና ቻይናዎች አረቦችና እሥራኤሎች አሜሪካና ጀርመን… እነሱስ ቢሆኑ …አንድ ሃይማኖት ብቻ ነው ያላቸው? አይመስለንም። ፪ የተለያዩ ቋንቋዎች ሕዝቡ በኢትዮጵያ ሰለሚናገር እኛን እንደ ጀርመንና እንደ አሜሪካን እንደ ሩሲያና እንደ ስዊስ „የሚያስተሳስር አንድ ቋንቋ በመካከላችን የለንም ።ስለዚህ ይህ እሰከ ሌለን ድረስ የጋራ ቋንቋ አለን ብለን መናገር እንችልም“ የሚሉ ሰዎች በየአለበት ይደመጣል። እሱስ ቢሆን እንደዚህ ዓይነቱ አባባል ዕውነት አለው ? ታሪካችን በብዙ መካራና ደስታ በክፉና በደጉ በውድቀትና በመነሳት በረሃብና በችግር በጥፋትና በልማት „የታጠረ“ ነው። ስለዚህ በዚህ መንገድም እኛን „….ታሪካችን አንድ ሊያደርግ አይችልም „ የሚሉ ሰዎች በመካከላችን አሉ። በደም ላይ ያልተገነባ በሠይፍና በጦር ያልተዋቀረ የአገር አንድነት፣ የመንግሥት አመሰራረት እንዲያው ዝም ብሎ የተሰባሰበ ግዛት በዚህች ዓለም ላይ አለ? 36