ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 32

ከአልጠፋ ነገር በአሁኑ ዘመን ማንሳት ተገቢ ጥያቄ ነው? ወይስ አይደለም?…ሥራ ከመፍታት የመጣ ፍልስፍና ነው ወይስ…ሊቀልዱብን ? ይህንንና ይህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን መጽሓፉን ፈጽሞ ያላገላበጠ ሰው በስህተት እንዲወረውር የተነሱት ጉዳዮቹ ሊገፋፉት ይችላሉ። በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እዚህ ጀርመን አገር ታትመው ገበያ ላይ የወጡት ሦስቱ መጻሕፍቶች በበርካታ ቃለ-ምልልሶችና አስተያቶችም በጋዜጣና በቴሌቪዥንና በራዲዮም ሪፖርታጅ ተደግፈውና ታጅበው የሰሚን ጆሮም አስደንቀዋል። አንዱ አዳኝ „እኔ መኖር እፈልጋለሁ። በጥይት መትቼ ገድዬ ጫካ ውስጥ የጣልኩትን የዱር እንስሳ ማታ ጠብሼ ስበላው ደግሞ ይህ ተፈጥሮ ነው ደስ ይለኛል።“ ሲል አንድ አታክልት ብቻ የሚበላ ሰው ደግሞ „የሰው ልጆች አውሬነት አይገባኝም…“ ብሎ ለአዳኙ ዓይነት ሰው መልሱን ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ሰጥቶአል። መስመር የለቀቀ ውይይት የተከፈተ ይመስላል። አንዳንዱ በሃይማኖቱ -ሕንድን ወይም ኢትዮጵያን ውሰድ- ሌላው በተፈጥሮው የተወሰነ ነገር ይበላል።የተቀረው ተጠይፎም ይሁን ነፍስ ያለው ነገር አልበላም ብሎ ከነገሩ ይርቃል። እነዚህ ጸሓፊዎቹ የወሰዱትና የሚከተሉት ፍልስፍና የወንድማማችነት የአብሮ አንዱ አንዱን ሳይበላ በሰላም ጉርብትና ላይ የተመሰረተ የፍቅር ኤቲክን ነው። ከዚያም አልፎ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከብቶችን ማራባት ማደለብ በጫጩቶቹ ላይ እንዳየነው እነሱ አያስፈልጉም ብሎ በመርዝ ጢስ መፍጀት ከእንደዚህ ዓይነቱ እርምጃ እንቆጠብ የሚለውንም ትችት ጽሑፎቻቸው ያነሳል። ወተት አንጠጣም አይብ አንብላም እንቁላል አንነካም ሌለው ቀርቶ ከበግና ፍየል ጸጉር የተሰራ ሹራብ አንለብስም የሚሉም አሉ። 32