ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 24

Animal Liberation የተባለው በPeter Singer ቀደም ሲል በ1975 ዓ.ም. የወጣው ተጨማሪ መጽሓፍ በአራተኛ ደረጃ ይጠቀሳል። ሁሉም በአንድነት „…ከብቶችን ማሰር እነሱን አሥሮ ማሰቃየት፣ መግረፍ ማደለብና አንድ ቀን ጎትቶ እነሱን ማረድ አርዶም መብላት ይህ ተገቢ ሥራ ነው ወይ? ለመሆኑ ይህን ለማድረግ ማን ፈቀደልን? በምን ምክንያት እኛ የሰው ልጆች እንደዚህ ዓይነቱን ` ፍጅት` በእንስሶች ላይ ለማካሄድ የተነሳነው? ይህንንስ ማድረግ እንችላለን ወይ?… ሕሊናችንስ አይወቀሰንም ወይ? ሞራላችን ይህን ይፈቅዳል? ኤትኩስ አያግደንም ወይ? ይህን ሁሉ ለማድረግ የሞራል በላይነታችን ይፈቅድልናል ወይ? „ብለው እራሳቸውን ጠይቀው በሺህ በሚቆጠሩ ገጾች ላይ መልሳውቸን አስፍረው እሱን ይዘውልን ቀርበዋል። …. ያለነውና አሁን የምንገኝበት ቦታ ግልጽ ለማድረግ የሞራልና የኤቲክ አንደኛው የፍልስፍና ዓለም ውስጥ ነው። C የቤት ሠራተኛን በጥፊ፣ አሽከርን በካልቾ፣ልጆችን በአርጩሜ፣ ተማሪን በአለንጋና በመጥረጊያ፣ሚስትን በቀበቶ መግረፍ መምታት መቅጣት እሷንም ሚስቴ ናት ብሎ አስገድዶ መተኛት በሕግ እዚህ የሚታወቀውን ለመድገም የተከለከለው ትላንትና ነው። ጊዜው እሩቅ አይደለም- ይህን የከለከለው ሕግ የወጣው- ያለፈው ክፍለ ዘመን በ20ኛው ላይ ነው። አሁን ደግሞ በዚህ በያዝነው 21ኛው ክፍለ-ዘመን -ነጮች ጠግበው የሚሰሩትን አጡ አይባል እንጂ- አንድ ሰው፣የቤት እንስሳውን የጋማና የቀንድ ከብቱን የውሻና የዶሮ ላባውን ጫፉን እንዳይነካ፣-ቢያንስ በጽሑፍ ደረጃ ኃይለኛ አስተያየቶች ተመራምረው ሰብስበው አሳትመው ጠርዘው ብቅ ብለዋል። በእንስሳና በሰው ልጆች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት የሚፈልግ አንድ ሰው በምንም ዓይነት ሳያነሳ ዘሎ ማለፍ የማይገባው ነገር/ነገሮች አሉ። 24