ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 23
እዚህ ለቤት ድመትና ለውሻ፣ ለቤት ወፍና የሳሎን ዓሣ በተቃራኒው
„ሰበአዊ የፍጡር መብታቸው“ – አትደነግጡ-„ ይከበር“ የሚሉ ሰዎች
ተነስተዋል።
እዚያ በአምላክ አምሳል የተፈጠረውን አንድን ሰው የመናገር መብቱን
ጉልበተኛ የታጠቀ ባለሥልጣን እንደ ጥጃ አለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝና አለ
ዳኛ ፍርድ የፈለገውን ያህል አመት ሊጠፍረው ይችላል።
አዳኞች ጫካ ወርድው አንድም ጥንቸል፣ አንዲት ወፍ ቀበሮና ተኩላ
አንበሳና አነር ዝሆንና አውራሪስ እንዳይገድሉ እዚህ „ይህን የሚያደርጉ
ግለሰቦች ይቀጡ ይታገዱ“ ይባላል።
እዚያ ! በጥላቻ ላይ ተመስርቶ ትላንትና የሚተዋወቅ ጎረቤት በጎረቤቱ
ላይ ጦር ሲመዝ አንዳንድ መንግሥታት ዝም ብለው ይመለከታሉ
ይባላል። በርቱ የሚሉም እንዳአሉ እዚህ ይጻፋል።
አይጦች ከላብራቶሪ እዚህ ነጻ ወጥተው ተለቀው „በሰላም እንደሌሎቹ
ፍጡሮች ይኑሩ“ ይባላል። እዚያ… በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ሰበአዊ
መብቶች አምኒስት እንተርናሺናል ሂውመን ራይት ወች በየጊዜው
እንደሚጽፉት „የሰው ልጆች መብት በእግር በደንብ ይረገጣል።“
ምን ዓይነት ዓለም ውስጥ ነው ያለነው?
B
ሦስት መጽሓፍት የእንስሳትን መብት አስመልክተው ገበያ ላይ በዚህ
በያዝነው ወር ወጥተዋል።ይህን ከሚሉት ሰዎች መካከል ፈላስፋዋና
ጋዜጠኛዋ የጀርመኑ ተወላጅ Hilal Sezgin (Artgerecht ist nur die
Freiheit. Eine Ethik für Tiere 301 Seiten.16,95 €)[i] በአንደኛ
ደረጃ ትገኝበታለች። ሁለቱ የአሜሪካን ፈላስፋዎችና ደራሲ Sue
Donaldson & Will Kymlicka[ii] በሁለተኛ ደረጃ አብረው እነሱም
ግሩም ሓሳባቸውን ይዘው ገባያ ላይ ቀርበዋል።
ሦስተኛው በFriederike Schmitz ተሰብስቦ የቀረበው „የእንስሳት
ኤቲክ“ የሚለው በአለ 589 ገጹ ወፍራም መጽሓፍ ነው።[iii]
23