ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር-07 | Page 22
እኩል መብት ለሁሉም ዜጋ
…ለሁሉም!
(ከስነ፥ምግባር / የሞራል ፍልስፍና)
„ጥያቄው ትልቁ ጥያቄ ! እንስሶች ያስባሉ ወይም አያስቡም የሚለው አይደለም? ወይም እንደ ሰዎች እነሱ ይናገራሉ
መናገርስ ይችላሉ? የሚለውም ጥያቄ ወሳኝ አይደለም። ትልቁ ጥያቄ እንስሶችን ሲጎዱአቸው ሲወጉአቸው ያማቸዋል
ወይስ አያማቸውም?… ውጋትስ ይሰማቸዋል ወይስ አይሰማቸውም ? የሚለው ነገር እሱ ወሳኝ ነው።“
Jeremy Bentham (1748-1832)
መገመት እንደሚቻለው የቤት እንስሳም የዱር አራዊትም ወፍና ትላትሎችም የወሃ ውስጥ ነፍሳትም ጭምር ሲወጉአቸው
ነፍስ ነውና እነሱም የያዙት አለጥርጥር ያማቸዋል። በአምላክ አምሳል የተፈጠረውን ሰው ደግሞ እነኳን መብቱን
ረገጠውበት በነገር ስያዋክትም የባሰ ያነገበግበዋል። (ከማስታወሻ ደብተሬ)
A
ቀጥሎ የምናነበው ታሪክና የምንከታተለው ፍልስፍና ቀልድም ፌዝም
የመድረክ ላይ ጨዋታ ሰው ማየት የሚፈልገውም ቲያትርም አይደለም።
ነገሩ-ጉዳዩን ለአልተከታተለው ሰው እንደሚመስለው – የአሽሟጦች
ቀልድም ሳይሆን በዕውነት ላይ የተመሰረተ የሞራል ፍልስፍና እና
ጥያቄም ነው።
እዚህ ከሰው መብት አልፈው ስለ እንስሶች መብት ማውራት ከጀመሩ አንዳዶቻችሁ በአካባቢአችሁ እንደሰማችሁት- ጊዜው ረዘም ይላል።
እንደምናውቀው እዚያ በአፍሪካ በአጠቃላይ ስለ ሰው ልጆች መብት
እንዳይነሳ በብዙ አካባቢ ከተከለከለ ቆይቶአል። እንዲያውም
እንደምናየውና እንደምናነበው ይህን ነገር አንስቶ መከራከር ያስቀጣል።
እዚህ ከአትላንቲክ ወዲህና ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወዲያ ለምንገኘው
ሰዎች ደግሞ ከእንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ „…ለጋማና ለቀንድ ከብቶች ሙሉ
የዜጋ መብታቸው በሕግ ይታወቅ“ ይባልላቸዋል።
እዚያ በአፍሪካ ዝም ብለህ አፍህን ይዘህ ተቀመጥ በየጊዜው ይባላል።
ቀደም ሲል ቅኝ ገዢዎች በሁዋላ እነሱን በተኩት አምባገነኖች ተደጋግሞ
እነደዚህ ዓይነቱን ነገር እንዳታነሱ ተብሎ ለብዙ ሰዎች ማስጠንቀቂያ
ተሰጥቶአል።
22