ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 47

የጓጓሁትን ያህል አሁን በእስተእርጅና ስለ የቀድሞ ጓደኞቼ ከአየሁዋአቸው ብዙ ዘመን ነውና ተቿኩዬአለሁ። በተለይ ያን የተማሪዎች መሰባሰቢያ አዳራሽ/አዳራሶች ከሁሉም በ1974 ዓ.ም (እአአ) የተሰበሰብንበት ሂትለር ያኔ ያሰራው ምናልባት ወደ አንድ ሺህ የምንሆን ወጣት የአውሮፓ ተማሪዎች ከየትነውየመጡት ከሞስኮ እስከ ፓሪስ ከለንደን እሰከ ስቶክሆልም ከለንደን እሰከ ሮም አምስተርዳም ካርቱም የተሰበሰብንበት የኦሎምፒክ ስታዲዮም(የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሲተላለፍ አንዴ አይቼአለሁ) እሱን እንደገና በሚቀጥሉት ቀናት ለማየት በጣም ጓጉቼ ነበር። ከዲዘርት በሁዋላ ነው የደፈረው ኮኟኩን ሌላው ውስኪውንና ጂንቶኒኩን አረቄውንና ኡዞውን የተቀሩት በዚያ ሙቀት የተቃጠሉት ደግሞ ወሃና ነጭ ወይናቸውን ከሲጋራቸው ጋር ይዘው ወደ ሳሎኑ ዘለቁ። ከብት የሚረባበት ወተት ያለበት አገር – እኛ እኮ ቻይና ወይም ጃፓን አይደለንም- ጣፋጩን አይስክርም መሥራት (ማቀዝቀዣውና የስኳር መሥሪያው ሸንኮራ እስካለ ድረስ ማንም የሚሰራው ነው። (ጣፋጭ ነገርን ከምግብ በሁዋላ- እንዲያው ታሪክን ለመጥቀስመቅመስን አውሮፓን ያስተማሩት ያስተዋወቁት ደግሞ -አያውቁትም ነበር ቱርኮች ናቸው። ስለዚህ የሰው ልጆች ሥራ ነው።) መለኪያዬን ይዤ እኔም አጥንቴ በዚያ የከተማ ዙረት መድከሙ የታወቀኝ ሶፋው ላይ ዝርግፍ ብዬ የተቀመጥኩ ሰዓት ነው። ድካም የጨመረብኝ የቤቱ ደረጃ ነው። ያን ረጅም ደረጃ ከተማይቱዋን ስቃኝ ረፍዶ ስለነበር- በዚህ ዕድሜዬ ረስቼው ነው እንጅ – ይህን አሁን ሳየው ማድረግ አይገባኝም ነበር – አንዴ ሮጬ ቁና ቁና መተንፈስ የጀመርኩት ከምግብ በፊት ነው። በሩን በፈገግታ የከፈቱልኝ ልጆች አስደንግጠውኛል። ከያዙት ሰታቴ ሳህን ላይ ይህን? ወይስ ይህን? ይውሰዱ ! ብለው ከማስተናገዳቸው በላይ ኮረዳዎቹ -አንዱዋ ነጭ ጠጉር አላት ሌላዋ ቀይ አንደኛዋ ጥቁርና አራተኛዋ በአለ ቡና ቀለም- በዕድሜአቸውም ~ 47 ~