ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 48

በቁንጅናቸውም በግልጽነታቸውም በአነጋገራቸው የቀድሞውን የወጣትነት ዘመኔን የሰባውን አመተ ምህርት የበርሊን ኑሮ እንዳለ አስታወሱኝ። ገጽታቸውና ፊታቸው በየዩኒቨርስቲው የምግብና የሌክቸር አዳራሽ በየሰላማዊ ሠልፉና በየቲች ኢኑ በ የመናፈሻውና በየቡና ቤቱ በተማሪዎች መኖሪያ ቤትና እነሱ በነበራቸው ቢራ ቤቶቹ በየመንገዱና ሱቁ ያኔ የማውቃቸው አብረውኝ ያኔ የነበሩ ተማሪዎች መሰለኝ። ዛሬ እነሱ የት እንዳሉ? ምን እንደሚሰሩ ጓደኛዬን እጠይቃለሁ ነገሩን አሳደርኩኝ። የጀርመኑን የቀዘቀዘ ነጭ ወይን ጠጅ „አመሰግናለሁ“ ብዬ በአልተረሳኝ ጀርመንኛዬ ከአንዱዋ ተቀብዬ አንድ ሁለት በረዶ እንዳይመታኝ ጣል አድርጌበት አምቦ ወሃ በላዩ ላይ ከልሼበት ወደ ውስጥ ጓደኞቼ ወደ ተቀመጡበት ሳሎን በሁለቱ ኮረዳዎች ታጅቤ እየተመራሁ ወደ ውስጥ ገባሁ። በ1999 ዓ.ም. (እ.አ.አ) ስድሳኛውን አመቱን ያከበረው እኛ ሁላችንን እንደገና የጋበዘን ወዳጄ መሓል ቆሞ ሰውን በሙሉ ከተለያዩ ቦታ የመጡ ስለሆነ እገሌ ሙያው… እንደዚህ ነው። እገሌ ደግሞ…የተማረው ይህን ነው…. እያለ ያስተዋውቃል። ~ 48 ~