ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 4

ኡምቤርቶ ኢኮ ያ „…በጽጌረዳ ስም..“ ብሎ ስለ አንድ የመካከለኛ ክፍለዘመን የገዳም መጽሓፍት ቤት ታሪክና የአርስጣጥለስ የፍልስፍና ትምህርቶቹ ተማሪዎች እጅ ገብቶ (በአውሮፓ) ከመንፈሳዊ ትምህርትና ከመልካም ሥራ ወጣት ልጆቹን አርቆ „እንዳያበላሻቸው“ እነሱን ስለሚጠብቀው አይነ ስውር ሊቀ ካህን በተረከው ትልቁ የልብ ወለድ ድርሰቱ ላይ አንድ ሰው የላበሪንት ገዳም- ሕንጻ ውስጥ ገብቶ እንዴት እንደሚወጣ በቀላሉ ያሳየናል። ብርድ የሚመክት ሹራብ ግን መልበስን ይጠይቃል። ደራሲው ይህንኑ ለወጣቱ አልብሶታል። ከአስተማሪው ጋር የአርስጣጥለስን መጽሓፍ የሚፈልገው ወጣቱ ልጅ የገባበት ሕንጻና እግሩ የረገጠው ክፍሎች ከነመስተዋቱ እያነጸባረቁበት ደረጃዎቹ መውጫና መግቢያውን ስለአዞሩበት ሽራቡን ሳያወልቅ ቀስ እያለ ተርትሮ እንደ መንገድ ቀያሽ መሓንዲስ በእሱ እየተመራ የት የት እንደ ነበረ ምንን እንዳለፈ በሚቀጥለው እርምጃ ምን ማድረግ እንደ አለበት ያ ልጅ በዚያች በለበሰው ሹራብ ጉዞውን ሊረዳ ችሎአል። መሓል ላይ የሹራቡ ክርስ ቢያልቅበትስ? የአዙሪት መናፈሻ ውስጥ ተገብቶ በቀላሉ የማይወጣበትን ጫካ እንደ ምሳሌ የወሰድነው አለ ምክንያት አይደለም። ውቅያኖስ ውስጥ ገብቶም ወዴት እንደሚዋኝ (ደሴትም መሬትም ተራራም በማ b