ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 3

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 ላቢሪንት/ፈሩ ሲጠፋ – ርዕሰ አንቀጽ ላበሪንት – የአዙሪት መናፈሻ ውስጥ ገብቶ መዝናናት -ውድ አንባባቢ- ቀላል ነው። ከዚያ ሳይረፍድ ወይም ሳይመሽ በቀላሉ መውጣት ደግሞ ከባድ ነው። አይቻልም። የገቡበት በር ይጠፋል።ያቋረጡት መንገድ አንድ ይመስላል። ግራ ቀኙ ተመሳስሎ ያደናግራል። የመውጫ በሩ እንደ መግቢያው አንድ ብቻ ነው። ታዲያ ከተገባበት መከራ መውጫ መንገዱ ብልሃቱ ምንድን ነው? ግንቡን በመሰላል መዝለል? ወይስ ወደ ላይ መንጠልጠል? ጫካ ውስጥ ቆሞ መጮህ?… በድፍረት መፏጨት? …መጸለይ? አንድ ተአምር ከላይ እሰከ ሚወርድ ቁጭ ብሎ መጠበቅ? ወይስ….? ደራሲዎች አእምሮአቸው ክፍት ስለሆነና ብዙ ነገር እነሱ በአንዴ ማየት ስለሚችሉ ቀላል መልስ መሰንዘር ይችሉበታል። ~3~