ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 18

ታሪክ ይቀጥላል።አለ ምክንያት አይደለም የኢትዮጵያ ታሪክም በአንድ ዘንዶ ታሪክ የሚጀምረው። በዚያ እንደ መስዋዕት በየጊዜው በሚቀርቡለት ሴቶችም ወንዶችም ልጆች በመብላት በአስቸገረው ዘንዶ ትረካ የሚጀምረው ታሪክ በንግሥና ይቀጥላል። በደፋሩ በአጋቦስ ብልሃትና ዘዴ ያ ወጣት ልጆችን በየወሩ የሚበላው ዘንዶው ይገደላል። አጋቦስ ሕዝቡ ቃል በገባለት ውል እሱ በኢትዮጵያ ላይ ይነግሣል። ልጁ ማክዳም ንግሥት ሳባ ተብላ አልጋውን ትወርሳለች። ሰይጣን አንዴ- በመጽሓፍ ቅዱስ- እባብ ተመስላ ብቅ ትላለች። ሌላ ጊዜ ሰይጣን ተቀይራ በ