ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 17

ለምንድነው ሕጻናት ክፋትን አያውቁም የሚባለው? ሰይጣን እነሱን (ሕጻናትን) ፈርቶ ሰለማይጠጋቸው ይሆን? አጋንንቶችና መናፍስቶች ልጆችን አይተው ሰለሚሸሹአቸው ይመስለናል? ሰይጣን ወይም መጋኛ ወይም አጋንንት.. ዲያብሎስ አተላ ይወዳል ይባላል። አመድ የሚፈስ ቦታ ይገኛል። በቀትር እየተዘዋወረ አላፊ አግዳሚውን ጫካ ውስጥ ይለክፋል ይባልለታል። ደም መጠጣት ይወዳል። ወንዝ ዳር ተኝቶ ድልድይ ሥር ተጋድሞ አድፍጦ ለቀም ለማድረግ ይጠብቃል ተብሎም ይነገርለታል። መብረቅ ሲመጣ ደንግጦ ሰው ላይ ይለጠፋል የሚሉ አሉ። …ፈሱም ኃይለኛ ሽታ አለው ይገማል ይባላል። የቬኑዙዌላ መሪ ሁጎ ቻንሰስ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ሚስትር ጆርጅ ደብሊዩ ቡሽን (ታናሹ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ላይ ንግግር አድርገው ሲወርዱ ተራውን ተቀብለው አትራኖሱ ጋ ሲጠጉ „ስለ ሰይጣን አንስተው አንድ ነገር ይሸተኛል…እሱ እዚህ ነበር። ጠረኑ የእሱ ነው ይሸታል…“ የሚለውን ቃላታቸውን ለመንግሥታት መሪዎች ወርውረው እኚህ ሰው አንዳንዶቹን ደጋፊዎቻቸውን እዚያው አስቀዋል። ሌሎቹን ደግሞ አስቆጥቶአል። ሰይጣን የሚባል ነገር ለመሆኑ አለ?ከአለስ የትነው ያለው? ወይስ ለማስደንገጥ ብቻ የሚነሳ ስም ነው? ለመሆኑ ሰይጣን ማን ነው? አዲስ ኪዳን „…ከከፉ ሁሉ ጠብቀን“ በሚለውአረፍተ-ነገር እንደጀመረው ሁሉ ብሉይ ኪዳንም ላይ ደግሞ „ ከዚህች ፍሬ አትብሉ …አለበለዚያ ክፉና ደጉን አውቃችሁ ትሞታላችሁ“ በተባለው የጥበብና የሕይወት ዛፍ ታሪክ የሰውን ልጆች ድራማ ይጀምራል። „…ዝምታው ምንድነው በጥሳችሁ ብሉ እንጅ! „ ብላ በመጀመሪያ ሔዋንን በሁዋላ አዳምን በተንኮል ምክርዋ በታለለቺው በዚያች እባብ ~ 17 ~