ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 16

እንቆጣጠረው ብሎ ተጣርቶአል። ምክንያት አለው ምክንያቱም ሰው ክፉም ደግም ነገር ለመሥራት ችሎታ ስለአለው ያለውም በመሆኑ ይህን እሱ ሼልንግ ተገንዝቦ አደገኛነቱን በዘመኑ ጠቁሞአል። ማሠሪያው ደግሞ ፍቅርና ሃይማኖት እንደሆነም አያይዞ ጽፎአል። ቶማስ ጄፈርሰን ነው የሰውን ልጆች ጎትቶ በመላእክቶችና በአጋንንቶች መካከል ያስቀመጠው። በአንድ በኩል የሰው ልጆች በእሱ ዓይን -ምንም እንኳን ጥሩ ሰው ለመሆን እንደ መላአክ በሥራቸው ለመምሰል ጥረት ቢያደርጉም- ሰዎች በምንም ዓይነት ቅዱሳን አይደሉም ይለናል። እትመኑአቸው ብሎም ያስጠነቅቃል። በሌላ በኩል የሰው ልጆች እንደ ከይሲው እርኩሱ ፍጡሮች ሰይጣኖች እንዳልሆኑም አንስቶ መልሶ ያጽናናል። እንግዲህ ሰይጣን አይደለንም። ግን ለምን የሰይጣን ሥራ በወንድሞቻችንና እህቶቻችን በጎረቤትና በዘመዶቻችን ላይ እንጠነስሳለን? ፈላስፋዎች እና ሳይኮሎጂስቶች „ሰዎች ሰይጣን አይደሉም „ስለዚህ የሰውን ልጆች ሁሉ ዝም ብለን በጭፍኑ ከማመን እጅና እግራቸውን በሕግና በሥልጣን ክፍፍል በትምህርትና በቅጣት ተብትበን እንያዝ አለበለዚያ አይቻሉም ይሉናአል። ጄፈርሰን ከቢጤዎቹ ጋር በዚያ የግለሰብን ነጻ-መብትን የሚያውቀውን የአሜሪካንን ሕገ-መንግሥት ሁለቱን „ቁጥጥርና ነጻነትን“ አጥምሮ አብሮ ነድፎአል ። ክፉና መጥፎ ሰው አለ። ለምንድነው አንዱ ሰው ክፉ ሌላው ርሕሩህ የሚሆነው? ክፉና መጥፎ ሰው ምንድነው?ምንድናቸው? ለምንድነው ክፋትና ጥፋት በእንስሶችና በልጆች ዘንድ ሳይሆን በሰው ልጆች ዘንድ ነፍሳቸውን በአወቁና ነገር በገባቸው ሰዎች ዘንድ በብዛት የምናየው? ክርስቶሰ እንደ ልጆች „ንጹሕ“ ሁኑ ብሎ ያስተምራል። ~ 16 ~