ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 15

ያኔ መጥተው ፍልስፍና እና አስተዳደር፣ ክርክርና ሪቶሪክ ሎጆክና ታሪክ በሚያስተምሩበት ዘመን የቤተ መንግሥቱ ቅጥር ግቢና የመሣፍንቶቹ ቪላ የወጣቶች መኮትኮቻ ትምህርት ቤት እንደ ነበር ተጸፎአል። ግሪኮች „ክፋትና የኃጢአት ሥራ“ ከአለማወቅ የሚመጣ ባህሪ ነው ይላሉ። ይህ አነጋገር ዕውነት ይሆን? ፈላስፋው ሆብስ ነው – ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን ሌሎቹን ከእሱ በፊት የነበሩትን አሰተማሪዎቹን ተከትሎ „…የሰው ልጅ አውሬ ነው። እንደ አውሬ እንድን ሰው እንድ ተኩላ አንድ ቀን አረሳስቶት ቦጭቆት የሚሄደው ያ ሰው እሱን የሚመስል ሌላ ሰው ነው።“ ከእሱና ከእነሱ እነሱንም ከሚመስሉ ተጠንቀቁ ብሎ ሌቪታን በመባል የሚታወቀውን መጽሓፉን እሱ ደርሶአል። ለጆን ሎክ ይህ መቦጫጫቅ እንዳይመጣ እሱ የሰጠው መልስ አጭር ነው። መቻቻልና የሌላውን አመለካከት አክብሮ ማዳመጥ መደማመጥ ዋና የመግባባት መነሻ ነው ይላል። እሱም ብቻውን በቂ እንዳልሆነም ያነሳል። አልፎም ሄዶ ሎክ ቁጥጥር እንደ ሌሎች ምሁሮች በሰው ላይ ማካሄድ ያስፈልጋል ይላል። በአራተኛው ክፍለ-ዘመን የተነሳው የክርስቲያና ሃይማኖት የሃዋሪያትን ወንጌል አስተማሪ የሰሜን አፍሪካው ተወላጅ አጉስቲኖስ ኢንስቲትውሽን -ተቋማት መዘርጋት አለበት ይላል። ለእሱ ለአጉስቲኖስ የሰው ልጅ በአውሬና በአምላክ መካከል የሚገኝ ሳይሆን በተፈጥሮና በአምላክ መካከል የሚገኝ ፍጡር ነው ይለናል። የሰውን ልጅ በአራዊትና በአምላክ መካከል በባህሪው የመደበው ሌላው ሰው የጀርመኑ ፈላስ ሼልንግ ነው። እሱም ተመራምሮ በደረሰበት ዕውቀቱ ይህን ፍጡር ሰውን ዝም ብለን አ